Hab Studio

Hab Studio

Share

18/05/2026

#እጅግ ልብ ይሰብራል !!

ሂንሴኔ ተፈሪ ትባላለች። ነዋሪነቷ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን፣ በ'ኒው ጀነሬሽን' ኮሌጅ የቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing) የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረች ሲሆን እጅግ ጎበዝ እና በውጤቷ ሌሎች ጭምር የሚቀኑባት እንደነበረች በቅርቧ ያሉ ይመሰክራሉ።

ሂንሴኔ ዛሬ እራሷን አጥ ፍታለች ።
ምክንያቷ ደግሞ የትምህርት ቤት ያልከፈለችው ክፍያ አስራ አምስት ሺህ (15,000) ብር እሷ ላይ የቀረባት ስለነበረ ነው። ክፍያ ያልፈጸመ ደግሞ የ'Exit Exam' ፈተና መፈተን ስለማይችል፣ ከጓደኞቿ መቅረቷ ተስፋ አስቆርጧት ህይወቷን እንድታጠፋ እንዳደረጋት ነው የተነገረው😥

Hab Studio

18/05/2026

የሄኒን ኢንተርቬው ሰማሁት። ሄኖክ በየዋህነት ተነሳስቶ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ "ህዝብ በገንዘቡ የሚሳተፍበት አንድ ፊልም" ለመስራት አልሞ የገንዘብ እርዳታ ጠየቀ። የጊዜው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ የትናንቱን መቶ ሺህ ብር ዛሬ የመቶ ብር ያህል እንኳ ዋጋ እያሳጣ ቃል የማያስጠብቅ ለዕቅድ የማይመች ሆኖ ፈረጃ የተባለውን ፊልም ለማውጣት ከህዝብ የሰበሰበው ሶስት ሚሊየን ብር የሶስት መቶ ሺህ ብር አሽቆልቁሎበት ክፉኛ ተሰቃየ።

ሄኖክ በቃለ መጠይቁ ላይ በሰፊው እንደ ገለጸው በእጅጉ የጎዳው የገንዘብ እጥረቱ ብቻ ሳይሆን የኛ ሰው "የሀበሻ" ኮሜንት (ዘለፋና ስድብ) ነበር። --- ገንዘብ ከለገሰው ይልቅ ዳር ቆሞ የተመለከተው ነበር በስድብ ሲያጥረገርገው የሰነበተው። ልጁ ግን ለአላማው ቁርጠኛ፤ ለቃሉም ታማኝ ነበርና ቃሉን በተግባር ተርጉሞ ፊልሙን ለእይታ አበቃ።
.. የኛ ሰው (ሀበሻ) እጅግ ከባድ (አስቸጋሪ) ከሚባሉ የአለም ህዝቦች ዋነኛው ይመስለኛል። ሰው ሲያገኝም ከስር ከስር መገዝገዝ፣ ቀን ሲዘምበትም ምሳር (መጥረቢያ) ይዞ ለመጣል መሯሯጥ። ....ይህ የሆነው ደግሞ በዚህ ዘመን የተፈጠረው (ቀለም ገብቶኛል፣ ሰለጠንኩ) ያለው ትውልድ በተነሳበት መሆኑ ደግሞ በእጅጉ አስገራሚ ነው።.....

ብቻ ሄኖክ ወንድሙ ለብዙዎቻችን በብዙ መልኩ ምሳሌ ሊሆን የሚችል አርቲስት ነው። ወንድማችን የሞራል ስብራት ሳይደርስበት፣ የማንም ስድብና ማጥላላት ተስፋ ሳያስቆርጠው ህልሙን ለስኬት ማብቃቱ በእጅጉ የሚደነቅ ምናልባትም በሲኒማው ኢንዱስትሪ ስሙን በደማቅ ቀለም ለመጻፍ የቻለ በመሆኑ ለአምስት አመታት የለፋበትን ፈረጃ ፊልሙን ለማየት እንጓጓለን!

Via: yetneberk tadele

17/05/2026

ይች የፕሮቴስታንት እህታችን ጎዳና ላይ እሰብካለሁ ብላ በምትጮህበት ቅጽበት አንድ አባት በመንገዳቸው ሲያልፉ ያገኟታል።አኒህም አባት መስቀሉን አውጥተው ሊባርኳት ሲሹ እሷም ወዳና ፈቅዳ በመስቀላቸው ስትባረክ የሚያሳይ ፎቶ ነው።በዚህ ምስል ላይ ከልጃቷ የተረዳውት አንድ ቁምነገር አለ።ይኸውም የእንጀራ ጉዳይ ሆኖባት እንጂ አንድ የገባት እውነት መኖሩን ነው።እሱም ቅዱስ መስቀሉ በረከተ ሥጋ ወነፍስን እንደሚያሰጥ።ከእውነት ጋር ተደብቆ መኖር ከባድ ነው።ለነፍስ እረፍትን ለአእምሮ ምቾትን አይሰጥም።የቱንም ያክል ልናስመስል ብንሞክር ከሕሊና ጋር ታግሎ ማሸነፍ እንደማይቻል ትልቅ ማሳያ ነው።
እህታችን ወደ እውነተኛይቱ ኦርቶዶክሳዊት ሕብረት ለመመለስ ያብቃት።

Via : መብሩክ

Photos from Hab Studio's post 16/05/2026

#ወደ ማርቆስ በረረ‼

ደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን በስኬት አስተናገደ‼

የአካባቢው ማኅበረሰብ ለብዙ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ ዛሬ በስኬት አስተናግዷል።

በዚህ ታሪካዊ ክስተት ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የከተማው አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች አውሮፕላን ማረፊያው መከፈቱ የደብረ ማርቆስንና አካባቢውን የትራንስፖርት ተደራሽነት ከማሻሻሉም በላይ የኢንቨስትመንት ፍሰትን፣ የንግድ ትስስርንና የቱሪዝም እንቅስቃሴን በእጅጉ ያፋጥነዋል ብለዋል። ነዋሪዎችም በበኩላቸው በልማቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸው፣ የአውሮፕላን ማረፊያው መከፈት ለወጣቶች አዲስ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። ይህንን ስኬታማ የሙከራ በረራ ተከትሎ በቀጣይ መደበኛ በረራዎች እንደሚጀመሩ ታውቋል።
ምስል ከደብረማርቆስ ከተማ ኮሙኒኬሽን የተወሰደ
የማርቆስ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ‼

15/05/2026

#ብዙዎች ፊቱን ሲመለከቱ በሳቅ ይፍነከነካሉ፤ ለ30 ዓመታት ዓለምን በሳቅ አዝናንቷል። ነገር ግን ብዙዎች ትክክለኛ ህይወቱ ምን እንደሚመስል አያውቁም። ይህ የሮዋን አትኪንሰን ወይም በመድረክ ስሙ ሚስተር ቢን አጭር አስተማሪ ታሪክ ነው።

እንደ ወሬ ነጋሪዎች ከአልበርት አንስታይን የሚበልጥ IQ እንዳለው የሚነገርለት ሮዋን ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግ ማስተርስ ድግሪ የተመረቀ ነው። የሚስተር ቢን መሆን ጉዞውም የተጀመረው እዚሁ ኦክስፎርድ በሚማርበትጊዜ ነው።

በዚያን ጊዜ እንኳን ሊያስቃቸው ይቅርና በመልኩ የተነሳ የክፍሉ ተማሪዎች 'ኤሌን ፊት' እያሉ ሙድ እየያዙ ይዘባበቱ እና ያበሽቁት ነበር። በተደጋጋሚ ለትወና በሚያመለክትበት ጊዜ 'በአግባቡ ለመናገር ያዳግተው ስለነበር/ይንተባተብ ስለነበር' በተደጋጋሚ አይሆንም ይባላል። የእነሱ እምቢታ ግን ወጣቱን ወደህልሙ ከመገስገስ እና ከመሞከር ሊያቆመው አልቻለም።

ከብዙ ሙከራ በኋላ አንድ ቀን መንተባተብ አቆመ። በትክክል ማውራት ቻለ። ስለሁኔታው ሲናገር፤ "አውነቱን ለመናገር መስታውት ፊት ቆሜ ፊቴን እየቀያየርኩ አልማመድ ነበር። እራሴን ሳይሆን ገፀባህሪውን ስሆን መናገር ቀለለኝ።"

ያም ሆነ በመልኩ/በፊቱ/ የተነሳ ማንም ሊያሰራው የሚፈልግ አልነበረም። ብዙ ቢሞክርም ጥረት እንጂ ውጤት ሊያገኝ አልቻለም፤ በትወና ብቻ ሳይሆን ህይወቱም ከበደበት፤ ሁሉም ነገር ካሰበው ጋር የሚሄድ ነገር የለም።

በመጨረሻም ወደ ራድዮ ጣቢያዎች ጎራ አለ። ለአስር አመታትም ፊቱን ሲያሳይ በድምፅ ብቻ Mr bean የተባለውን ገፀባህሪ እየተጫወተ አሳደገው። በመጨረሻም ሚስተር ቢን በስሎ ከአስር ዓመት በኋላ ወደ ቴሌቭዠን በአካል መጣ።

ሚስተር ቢን መታየት ሲጀምር ሁሉም በአድናቆት መሳቅ ጀመረ...ለሮዋንም የአለም አቀፍ እውቅና እና ዝና አተረፈለት። በመጀመሪያ የተጠላበትእና የተነቀፈለት ፊቱ ለስኬቱ ቁልፍ ሆነ።

ብዙዎች እንደሚሉት ከችግሮቻችን እንደምንልቅ ችግር ነው ያልናቸው ነገሮች ወደ ስኬት ሊመሩን እንደሚገባ ያሳየ ስመጥር ሰው ሆነ።

የሚወረወርብህን ድንጋይ ሰብስበህ በሱ ቤት መስራት ወይም ዘላለም እያለቀሱ መኖር የቱ እንደሚሻል ያሳየም ሰው ነው።
ከማህበራዊ ሚዲያ ሳነብ ያገኘሁት ነዉ።

fans
Hab Studio

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa