A B pharmacy
ኩላሊትን የሚጎዱ ልማዶች እና የኩላሊት ህመም ምክንያቶች
አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ?
ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም
1) የደም ግፊት (Blood pressure) አለመቆጣጠር
2) የስኳር ህመም ምርመራ (Fasting blood sugar) አለማድረግ እና በየጊዜው ክትትል አለማድረግ
3) የኩላሊት ኢንፌክሽን በግዜው አለመታከም።
4) ሽንትን መቋጠር
ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል።
5) በቂ ውሃ አለመጠጣት
አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት።
6) ጨው ማብዛ(በተለይ ደም ግፊት ላለባቸው ሰዎች)
ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል።
7) የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር
የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ።
8) Alcohol መጠጥ ማብዛት
መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል።
9) ሲጋራ ማጨስ
በመጨረሻም ለኩላሊታችን ትልቅ ጥንቃቄ ልናደርግ ና ከላይ የተዘረዘሩትን የሃኪም ምክሮች በአግባቡ በመተግበር የኩላሊታችንን ጤና መጠበቅ እንደሚያስፈልገን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር መስቀሌ ቢረዳ አሳስበዋል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
14/01/2025