Christ Embassy Church - Summit 72

Christ Embassy Church - Summit 72

Share

20/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Wednesday 20, May 2026
ረቡዕ፣ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ሰይጣናዊ ተፅእኖዎችን ቆርጣችሁ ጣሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ በርያሱስ የሚሉትን ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የሆነውን አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ (የሐዋርያት ሥራ 13:6)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════

የሐዋርያት ሥራ 13፣ ሰይጣን ወንጌል ወደሰዎች በተለይም በመሪነት ስፍራዎች ላይ ወዳሉት ሊደርስ ባለበት ጊዜ፣ እንዴት ለመቋቋም እንደሚሞክር ግልፅ የሆነ ማሳያን ይሰጠናል። ሳኦል (ጳውሎስ) እና በርናባስ ወንጌልን በመስበክ በጳፉ ደሴት ባለፉ ጊዜ፣ የሆነው በሐዋርያት ሥራ 13:6 ላይ እንደምሳሌ ሆኖ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ "አስተዋይ ሰው" ብሎ የሚገልፀው አገረ ገዥ ሰርግዮስ ጳውሎስ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ፈልጎ በርናባስና ሳኦልን (ጳውሎስን) አስጠርቶ ነበር (ሐዋርያት ሥራ 13:7)። ስለኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ማወቅ ፈለጎ ነበር።

ነገር ግን ያ እንዲሆን ያልፈቀደ ከእርሱ ጋር በቅርበት የተገናኘ አንድ ሰው ነበር፤ ይህንን የሐዋርያት ሥራ 13:6-8 የአምፕሊፋይድ ክላሲክ ትርጉም ይገልጠዋል: "የቆጵሮስን ደሴት ከዳር እስከ ዳር አቋርጠው ጳፉ በደረሱ ጊዜ፣ በርያሱስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ጠንቋይ ወይም አስማተኛና ሐሰተኛ ነቢይ አገኙ፤ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው ብልህና አስተዋይ አገረ ገዥ ጋር በቅርበት ነበረ። ይህ አገረ ገዥ፣ [በክርስቶስ ስለሚገኘው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ስላለው መዳን] የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን አስጠራቸው። ጠቢቡ ሰው ኤልማስ ግን፣ [እራሱ ለራሱ የሰጠው] የስሙ ትርጒም እንዲህ ነበርና፣ አገረ ገዡ እምነቱን እንዳይቀበል ለማደናቀፍ ስለ ፈለገ ተቃወማቸው።" መሪው የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይቀበል በመቋቋም ለማስቆም ሞከረ።

ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ "ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ሲመለከተው። አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? ...አለው" ይላል (ሐዋርያት ሥራ 13:9-10)። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረው በጥርጣሬ ወይም በስሜት አልነበረም። የተናገረው በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት ነበር። የዲያቢሎስ ልጅ፤ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሲል እውነተኛ በሆነው ማንነቱ ጠራው።

በብዙ የአለም መሪዎች ዙሪያ እንዲህ ያሉ እውነትን የሚያጣምሙና የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይሰሙ የሚከላከሉ ሰዎች አሉ።
በጸሎት የምንቆመው እንዲህ ያሉ ሰዎችን ተፅእኖ ከሃገራት መሪዎች ላይ የምንቆርጠው በዚያ ስለሆነ ነው።

በተደጋጋሚ፣ በአለም ዙረያ ላሉ ለሃገራት መሪዎች፣ ለመንግስታትና ለተቋሞች ስትጸልዩ፣ የዚህ አለም "ኤልማስ" ምክሮች ከንቱናድምጽ አልባ መሆናቸውን አ ውጁ፤ ከመሪዎች ላይ ያላቸውን ተፅእኖ ቁረጡ። በአለም ዙሪያ ሁሉ የፕሬዝዳንቶች፣ የነገስታት፣ የገዢዎች፣ የህግ አውጪዎችና የውሳኔ አስተላላፊ ሰዎች ልቦች የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማትና ለመቀበል ክፍት እንዲሆኑና ወንጌል በሕይወታቸው ላይ ውጤት እንዲያፈራ ጸልዩ።

እንዲሁም ወንጌል መሰበክ እንዲችል፣ ሰዎችም በነፃት መቀበል እንዲችሉና በአለም ዙሪያ ሁሉ በፍጥነት እንዲስፋፋ መንፈስ ቅዱስ ሽንገላን የመለየት አስተውሎት እንዲሰጣቸውና የጽድቅ ተፅእኖዎች እንዲከቧቸው ጸልዩ። ሃሌሉያ!



የእምነት አዋጅ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በሃገራት ውስጥ ባሉ መሪዎችና ውሳኔ አስተላላፊዎች ልቦች ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ እንዲያይል እጸልያለሁ። ወንጌልን የሚቋቋምና ከእውነት የሚመልሳቸው እያንዳንዱ የሰይጣን ተፅእኖ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተቆረጠ ነው። የእግዚአብሔር ጥበብና ጽድቅ ሃገራትን ይገዛል፤ እውነቱም ያለተቋቋሚ ተመስርቷል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ 2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 15:31
├─ መዝሙረ ዳዊት 33:10
├─ መጽሐፈ ምሳሌ 21:30
└─

━━━━//━━━

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Summit 72
Addis Ababa
1000