Hanos Media and Promotion
24/01/2026
ዜና ችሎት :- የሞት ፍርድ ተፈረደባት::
በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳሽ የነበረችው ሰንበቴ ታደሰ ጥፋተኛነቷ በፍርድ ቤት ተረጋግጦ በሞት እንድትቀጣ ተወሰነባት።
ውሳኔው የተሰጠው በትናንትናው ዕለተ አርብ ጥር 15/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ፍርድ ቤቱ መግለጫ፣ ተከሳሿ በ2017 ዓ.ም በኮቸሬ ወረዳ ውስጥ በተፈፀመ ከባድ የወንጀል ድርጊት ተከሳሽ ሆና ቀርባ ነበር። ክሱ በ1997 ዓ.ም የወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1(ሀ) መሠረት ቀርቦ ተመርመሯል።
ተከሳሿ በችሎቱ ፊት ወንጀሉን እንዳልፈፀመች በመከራከር ቆይታ አድርጋ ቢሆንም፣ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የቀረቡ ማስረጃዎች በፍርድ ቤቱ በቂ መሆናቸው ተገምግሟል። ተከሳሿም ተጨማሪ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻለች በፅሁፍ አሳውቃለች።
በዚህ መሠረት፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ከፍተኛ ክብደት ያለው እና ሕጉን በግልፅ የሚጥስ መሆኑን በመግለጽ፣ ተከሳሿ በሞት እንድትቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።
ከችሎቱ ታዳሚዎች መካከል አንዳንዶቹ፣ ውሳኔው ሕግን ለማስከበር እና ለማስጠንቀቅ አስፈላጊ መልዕክት አለው ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።
Via የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት – ህዝብ ግንኙነት
24/01/2026
"ከአርሰናል ጋር ያለን ጨዋታ በእርግጠኝነት ከባድ እንደሚሆን ይታወቃል፤ ሆኖም እኛ በጥሩ ብቃት ላይ እንገኛለን።
ወደ ኤምሬትስ የምናመራው ሶስቱንም ነጥቦች ይዘን ለመውጣት ነው። በመልሶ ማጥቃት ስራቸውን በአግባቡ የሚወጡ ፈጣን የክንፍ ተጫዋቾች ስላሉን፣ የእነሱን ተከላካይ ክፍል ሰብሮ መግባት ለእኛ ፈተና አይሆንም።" ፓትሪክ ዶርጉ
23/01/2026
🎙 “ አርሰናልን ለመግጠም ጓጉቻለሁ “ ማይክል ካሪክ
የማንችስተር ዩናይትዱ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ለአርሰናል ጨዋታ " በጣም ጓጉቻለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።
“ አርሰናል ምርጥ ቡድን ነው “ ያሉት ማይክል ካሪክ “ ብዙ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች አሏቸው ትልቅ ፈተና ነው “ ብለዋል።
ጨዋታውን በቀላሉ እንደማይመለከቱ የገለፁት አሰልጣኙ “ ነገርግን በጥሩ መልኩ መመልከት አለብን " ሲሉ ገልጸዋል።
ስለ ቡድናቸው ያነሱት ካሪክ “ አንድ ጨዋታ ብቻ ምርጥ ቡድን አያደርግም ነገርግን ጥሩ መሰረት ይሆነናል “ ሲሉ ስለ ደርቢው ድል ተናግረዋል።
“ በቡድኑ ውስጥ ጥሩ ድባብ አለ ነገርግን ከፊታችን ምን እንዳለ እናውቃለን በራስ መተማመን እና በትኩረት መካከል ሚዛን ማግኘት አለብን " ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
" የትኛውም ውሳኔዬ የአጭር ጊዜ አይደለም ፤ ክለቡ በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆኖ የማስረከብ ሀላፊነት አለብኝ። “ ማይክል ካሪክ
Click here to claim your Sponsored Listing.