R.I.P
25/04/2021
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
********************
አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በኮቪድ-19 ምክንያት በተወለደ በ50 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።
አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።
28/03/2021
መጋቢት 18/1980
በማይረሳ ታለቅ ተጋድሎ ህይወታቸውን በጀግንነት የሰጡን ኢትዮጵያዊ ጀግና ብርጋዴር ጄነራል ለገሠ እበጄ የመስዋዕትነት ቀን!!
እኔ እኝህን የሀገራችንን ታላቅ ሰው ብርጋዴር ጄነራል ለገሠ አበጄን በቅርበት ለማወቅ ዕድል ካገኙ ሰዎች መካከል አንዱ በመሆኔ ሁሌም ኩራት ይሰማኛል::
ጄነራል ለገሠን የማውቃቸው ኤርትራ ክ/ሀገር / ሰራዬ አውራጃ /መንደፈራ በኮሎኔልነት ማዕረግ የ 503ኛ ሀ ንዑስ ግብረ ኅይል አዛዥ በነበሩበት ዘመን ነው::
ጄነራል መኮንኑ በህይወት ዘመኔ ፍፁም እንዳልረሳቸው ሆነው በአዕምሮዬ ውስጥ ከገዘፉ ምርጦቼ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ናቸው::
አፍላ ጎረምሳ በነበርኩበት ዘመን ሁለት ጊዜ ማሰብና አዙሮ ማዬት የሚባለውን የህይወት ቁልፍ ነጥብ የተማርኩት ከእሳቸው ነው::
በአዘቦታዊ የኑሮ ዑደት ውስጥና በእኔ የስቪል ህይወት ውስጥ በእርጋታ አስቦ በአስተውሎት ለመወሰን የእሳቸው ተምሳሌት ቀላል አልነበረም::
በፈታኝ ወቅቶች ያለማወላወል...የአስቸኳይ እርምጃና የቁርጠኛ ውሳኔ አስፈላጊነትን በእርሳቸው ወታደራዊ አመራርና ድልአድራጊ አዋጊነት በፀጥታ ተምሬያለሁ::
ከዕዝና አስተዳደራዊ ተፅዕኗቸው ውጭ ካለው ማህበረሰብ ጋር በተግባቦት ለመኖር ይፈጥሩት የነበረው የሠላማዊ ወንድማማችነት የአኗኗር ስልት ዛሬም አብነቱ ህያው ሆኖ አብሮኝ ይኖራል::
ለእኔ ብርጋዴር ጄነራል ለገሠ አበጄን ያህል ታላቅ ሰው ማወቅ.....ስለእሳቸው መናገርና ዕማኝ መሆን መቻል ልዩ ክብርን ይሰጠኛል:: በግዙፍ ዋርካ ስር የመጠለል አይነት ምቾትም ይሰማኛል::
ለሀገር ክብር ለታሪክና የወገን ፍቅር ሲባል በጠላት ፊት ከመንበርከክ ይልቅ እንደታላላቆቹ የሀገራችን ባለታሪኮች ሁሉ ሽጉጣቸውን የጠጡት ብርጋዴር ጄነራል ለገሠ አበጄ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን የከፈሉልን ህያው ባለውለታችን ናቸው:: ገድልና ታሪካቸውም በኢትዮጵያውያን የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል!!
ነፍስ ይማርልን‼️
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
251