Arada Woreda five communication office

Arada Woreda five communication office

Share

Photos from Arada Woreda five communication office's post 08/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ጷጉሜ 3 «የፅናት ቀንን»አስመልክቶ የስነ ፅሁፍ ምሽት ተካሄደ
አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ኮሙኒኬሽን
ጰጉሜ 3/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ጷጉሜ 3 «የፅናት ቀንን»አስመልክቶ ከተለያዩ የአመራር እርከኖች የተወጣጡ አካላት በተገኙበት አነቃቂ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ተካሄደ።
​በምሽቱ መርሃ ግብር ላይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘዉ፣ እንዲሁም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።በመድረኩ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ ጉባኤየሆኑት አቶ ደሳለኝ አገኘዉ ባስተላለፉት መልእክት፤ ፅናት ለማንኛውም ሀገራዊና ማህበራዊ ስኬት፣ ለልማት እንዲሁም ለህዝቦች አንድነት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። አክለዉ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መንገሻ ሲሳይ እንደገለፁት መሰል የሥነ-ጽሑፍና የባህል መድረኮች በህብረተሰቡ ዘንድ የመደጋገፍ፣ የፅናት እና ወንድማማችነትን ባህል ለማሳደግ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
​በዝግጅቱ ላይ የጷጉሜ 3 «የፅናት ቀን» ትርጉምና ሀገራዊ ፋይዳን የሚያጎሉ፣ የህዝብን የፅናት ጉዞ የሚያስሱ ግጥሞች፣ አጫጭር ወጎችና ልዩ ልዩ የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች ለታዳሚው የቀረቡ ሲሆን፤ ምሽቱም በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

Photos from Arada Woreda five communication office's post 20/08/2026

"ሰላም የወል ሀብታችን፣ የዕድገታችን መሰረት በመሆኑ ጥበቃውም የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው!" - አቶ ወንድሙ ኡመር

​አራዳ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ባለፉት 10 ቀናት ያሰለጠናቸውን 869 የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር ሰላም የዕድገትና የልማት መሰረት መሆኑን ገልጸው የሰላም ሰራዊቱ ህዝብን ከአደጋ የሚጠብቅና ከመደበኛ የፀጥታ አካላት ጋር የሚቀናጅ የህዝብ አለኝታ መሆኑን አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ተመራቂዎች ከሀሰተኛ ወሬዎችና ውዥምብር ነፃ በመሆን በአካባቢ ጥበቃ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል።

የሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ዶጃ በበኩላቸው ክፍለ ከተማዋ ሰላሟ ተረጋግጦ እንድትቀጥል የሰራዊቱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ተመራቂዎች የ10 ቀን ወታደራዊና የንድፈ-ሀሳብ ስልጠና ወስደው ቃለ-መሀላ የፈጸሙ ሲሆን የመታወቂያ ካርድና የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

​በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 5 ዓመታት ከ200,000 በላይ የሰላም ሰራዊት አባላት የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማም ከ9,000 በላይ ነባር የሰላም ሰራዊት የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተመረቁት 869 አባላት ነባሩን ሰራዊት የሚቀላቀሉ ይሆናል

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 19/02/2026

Website

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada Woreda five communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.