Bole 05 communication

Bole 05  communication

Share

23/04/2026

ከብዙ ወደ አንድ ፣ አንዱም ፣ ወደ-እያንዳንዱ ቤት!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “በአዲስ መሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል በተንቀሳቃሽ አውቶቢስ የሚሰጡ 8ቱ አገልግሎቶች “

- የገቢ አገልግሎት (አዲስ ቲን ማውጣት)
- የንግድ አገልግሎት (ንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ ማደስ)
- የጤና (ለመንጃ ፈቃድ አካላዊ የጤና ምርመራ)
- የሲቪል ምዝገባ (መታወቂያ፣ ልደት እና ሌሎች)
- የአሸከረካሪ ተሽከርካሪ (የመንጃ ፈቃድ እና የቦሎ ዕድሳት)
- የኢትዮ ፖስታ (የመንገድ ፈንድ ክፍያ)
- የብሔራዊ መታወቂያ (አዲስ ምዝገባና የመረጃ እርማት)
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (ቅድመ ክፍያ)

Photos from Bole 05  communication's post 22/04/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኪነ-ጥበብ ምሽት ተካሄደ።

"አስተሳሳሪና የወል ትርክታችን ለዘላቂ አንድነት እና አብሮነታችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የኪነ-ጥበብ ምሽት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እንዲሁም የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አለምጸሀይ ሽፈራው በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማዋ እየተመዘገቡ ያሉ የልማት ስራዎች የለውጡ አመራር ለህዝቡ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ኪነ-ጥበብ ህብረተሰቡን ለማስተማር ብሎም ለማዝናናት ካለው ሚና ባሻገር አስተሳሳሪና የወል ትርክታችን ለዘላቂ አንድነትና ለአብሮነታችን መጠናከር ያለውን ፋይዳ ሚናው የጎላ ነው" ብለዋል። አርቲስቶችና የጥበብ ባለሙያዎችም ህዝቡን ለሰላምና ለልማት ለአንድነት በማነቃቃት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ-አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው፤ ክፍለ ከተማው ከማህበራዊ አገልግሎቶች ጎን ለጎን ለኪነ-ጥበብ ስራዎች ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸው፣ የዛሬው መርሐ ግብር የከተማና የክፍለ ከተማ አስተዳደሩን የተቀናጀ አሰራር የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። አቶ አደፍርስ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍልና አመራሩ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር፤ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጎብኚዎች ደግሞ ሳቢ የማድረግ ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። "የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መሪነት የለውጡ አመራሮች ሌት ተቀን በመስራታቸው፣ አዲስ አበባ ዛሬ ላይ ውብ፣ ማራኪና አበባ ሆና የቱሪዝም ማዕከል መሆን ችላለች ሲሉ ኃላፊው በተጨማሪ ገልጸዋል።

በመድረኩ በአዲስ ዩኒቨርስቲ የቲያትርና ጥበባት ክፍል የተዘጋጀ ሙዚቃዊ ተውኔት ለታዳሚዎች ቀርቧል።

ቦሌ ኮሙኒኬሽን
ሚያዝያ 14/2018

15/04/2026

የምርጫ ካርድ ወስደዋል?

ባሉበት ሆነው በ*ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።

የዛሬው ካርድዎ የነገዋን ታላቂቷን ኢትዮጵያ መገንቢያ ዋነኛ መሣሪያ ነው!የምርጫ ካርድ ወስደዋል?

ባሉበት ሆነው በ*ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።

የዛሬው ካርድዎ የነገዋን ታላቂቷን ኢትዮጵያ መገንቢያ ዋነኛ መሣሪያ ነው!

Photos from Bole 05  communication's post 26/03/2026

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ "Invest in Ethiopia 2026" የኢንቨስትመንት ፎረም ተሳታፊዎች የዓለማቀፍ ኮንፈረንስ ማዕከልነቷን በተግባር እየገለጠች የመጣችውን ውቢቷ ከተማችን አዲስ አበባን ጎበኙ።

ከ 71 በላይ ሀገራት በሚሳተፉበት የ"Invest in Ethiopia 2026" ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለመሳተፍ የመጡ ባለሀብቶችና በዘርፉ የተሰማሩ ተዋናዮች፣ በመዲናዋ ያለውን ፈጣን የዕድገትና የልማት ስራዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል።

ከ800 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፖሊሲ አውጪዎች የሚሳተፉበት ይህ የቢዝነስ ፎረም በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል በይፋ ተጀምሯል።

Addis Ababa Tourism Commission

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Megenagna
Addis Ababa