Green Time

Green Time

Share

28/05/2022

Brand New
sandisk Flash
Size #32 GB
Price 500
Phone +251930399323
በራሳችን ትራንስፖርት ባሉበት እናደርሳለን

29/12/2021

እስቲ የእስካሁኑ ይብቃንና እንዲህ ይመርብን

Photos from Green Time's post 09/12/2021

ወፍ ዘራሽ አይደለሁም!

ወፍ ዘራሽ አይደለሁም! የበቀልኩበትን፣ ያጌጥኩበትን፤ ደግሞም ያሸበረቅኩበትን አውቃለው።በራሱ ቀለም ነክሮ የገዛ ቀለሙን ያዋሰኝን አሳምሬ አውቃለው። ዛሬ ደረሶ ፊደል ብቆጥር፤ ባህር ተሻግሬ፣ አድማስ አሳብሬ የጎረቤት አደራረግን ብቀስም የእውቀት ቀንዲል አያደርገኝም።

ከኖረበት ምድር ጥበብ የተዋሰ፤ ከሰንበተበት መስክ ማስተዋል የቀዳ፤ ከፈለቀበት ሸንተረር ወግ እና ልማድ ያዋደደ፤ ከጠጣው ኩሬ የኑባሬን ጠሊቅ ሚስጢር የቀመረ፤እትብቱን ከቀበረበት አፈር ብሂል ያዋለደ፤ ካደመጠው የንጋት ዜማ ኪነት ያበለጸገ፤ እውነቱን፣ ገድሉን፣ ሰቀቀኑን፣ ናፍቆቱን በልሳን የከተበ ፤በዜማ የሰደረ ህዝብ ነው ያፈለቀኝ። እርሻን ከሚያውቅ ገበሬ፣ ከብትን ከሚያውቅ እረኛ፣ ሰብራት ከሚጠግን ወጌሻ፣ ቅጥል ከሚጨፈልቅ ቀማሚ ነው ልደቴ። እድገት መሰረቴ። አፈርን ከሚያውቅ ሸክላ ሰሪ፣በገናን ከሚቃኝ ባለ ቅኔ፣ ህልምን ከሚፈታ አዋቂ ነው ስሪቴ። የህይወት ትምህርቴ።

ያበቀለኝ ህዝብ ፍጹም ባይሆንም በሁሉ የነሆለለም አይደለም። እክል እና ግድፈት ባያጣውም ከእውቀት ተፋቶ ጨለማ ብቻ የተጣባውም አይደለም።እጅና ጉልበት ስሞ፣እግር አጥቦ ሰውነትን ያስተማረኝ ይኽ ህዝብ ነው። ፊደሉን፣ ዜማውን፣ ፈሊጡን፣ ብሂሉን ላዋሰኝ፤ ሰው አድርጎ ለሰራኝ ህዝብ የእድሜ ዘመን ባለእዳ ነኝ። ወፍ ዘራሽ አይደለሁማ!!!

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa