Desta kussa ye Itiye lij
05/11/2025
አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል -የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ
ወላይታ ሶዶ፤ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም በክልሉ አዲሱ የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቅር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተጠቁሟል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የወላይታ ሶዶ ክላስተር ማዕከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ ፣መንግስት የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ ለመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቁመዋል።
ይህንኑ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ፣ ክፍያውን ለመፈፀም የሚያግዙ መረጃዎች በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በመግባት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኑሮ ማሻሻያ ቋሚ፣ መደበኛና ጊዜያዊ የመንግስት ሰራተኞችን እንደሚያካትት ገልፀው ፣ክፍያው በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቀር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በታችኛው መዋቀሮች አልፎ አልፎ የመረጃዎች ክፍተቶች ስለመኖራቸው የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፣ይህም በአጭር ጊዜ ተሟልተው ለክልል ፋይናንስ ገቢ ሆኖ ክፍያ ይፈፀማል ብለዋል።
በተወሰኑ በታችኛው መዋቀሮች ደመወዝንና ደረጃን በትክክል የሚገልጹ የመረጃ ክፍተቶች እንደ ችግር መታየቱን ጠቁመው ፣ይህንኑ የማጥራት ስራ እየተፋጠነ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አዲሱን የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፤ ማህበረሰቡ በሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
#ምንጭ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ
ኸረ ጆሮ ያለው መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ሶዶ ላይ ያላቹ ወይ ደረሰኝ አይቆረጥ። መነሐሪያ በጠራራ ፀሐይ ዝርፊያ እየተካሄደ ነው ካልሰማቹ ስሙ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
SODDO