Ethio channel
08/02/2022
አይ ሳሮን
27/01/2022
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከእነመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
መነሻውን ከአማራ ክልል ባህርዳር ልዩ ዞን ባህርዳር ከተማ ባደረገ አይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጭነው አዲስ አበባ በማስገባት ለሽያጭ ሲያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ሶስቱ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በአይሱዙ ውስጥ ሻግ በመስራትና በውስጡ በማድረግ በቁጥር አምስት ሺህ ስድስት መቶ አስር የሚሆን የክላሽ ጥይት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲገባ አድርገዋል።
ግለሰቦቹ ይህንን መሳሪያ ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲሉ በተደረገ ክትትል የጦር መሳሪያውን (ጥይቱን) ጨምሮ ሶስቱም አዘዋዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢፕድ ምንጮች አስታውቀዋል።
19/01/2022
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕክምና ላይ የሚገኘውን አርቲስት አሊ ቢራን ጠየቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በዕለተ ጥምቀት በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል በሕክምና ላይ የሚገኘውን አንጋፋውን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን ጠይቀዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተዋል (ኦቢኤን)
Click here to claim your Sponsored Listing.