I Hope

I Hope

Share

09/02/2026

ኢትዮጵያን ወግቶ አሸናፊ መሆን አይቻልም"

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

09/02/2026

ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ስታሳይ ፣ ኤርትራ ግን ቀጠናውን የማተራመስ ፍላጎቷን በግልጽ አሳይታለች !!

ገንቢ የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥርጣሬና የተሸሸጉ ፍላጎቶችን በመፈለግ ላይ ሳይሆን ፣ ትኩረትን ዋና ዋና የቀጠናው ጉዳዮች ላይ በማድረግ ችግሮችን መፍታትን ይጠይቃል።
ኢትዮጵያ ይህንን መርህ መሠረት በማድረግና ለቀጠናው ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ፣ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመጨረስ ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ደብዳቤ ብታሳውቅም ፣ በኤርትራ በኩል ግን ለቀረበው የሰላምና የውይይት ጥሪ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጉዳዩን ወደ ጎን በመተው ለውይይት ዝግጁ አለመሆኗን በግልጽ አሳይታለች።

ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ለመሳተፍ ያላትን ዝግጁነት እየገለጸች ባለችበት በዚህ ወቅት ፣ የኤርትራ እምቢተኝነት በቀጠናው የተረጋጋ ግንኙነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍና ሃገሪቱ ለሰላማዊ አማራጮች ያላትን ዝቅተኛ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ የሻዕቢያ መንግስት ለቀጠናው አለመረጋጋት ዋና ተጠያቂ የሚያደርግ ነው።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Website

Address

Ethiopia
Addis Ababa