Hashkey fantastic
01/02/2023
ትምህርት ሚኒስቴር፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50% በታች ያመጡና በዩቨርሲቱ የቅበላ አቅም " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " 10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሄንን ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን። በ10 ቀን ውስጥ የትኞቹ ተማሪዎች ዕጩ በመንግስት ተቋማት ሄደው እንደ ስኮላርሺፕ ተማሪ ዶርም ይዘው ምግብ ቀርቦላቸው በቅተው ለሚቀጥለው ዓመት ፌሬሽ ማን የመሆን ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በሌሎች አማራጮች ይማራሉ የሚለውን ጉዳይ ቢገፋ በ10 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን በጣም ቢገፋ በ15 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን " ብለዋል።
" ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የታወቀው።
ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች በግል በመፈተን ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችል ውጤት ማምጣት / በፍላጎት እና ምርጫ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መውሰድ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| 09:00 - 17:00 |