AAU Fast Information

AAU Fast Information

Share

Photos from AAU Fast Information's post 28/06/2026

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 417 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው ለ76ኛው ዙር ያስተማራቸውን 3 ሺህ 542 ተማሪዎቸ‍ን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 2 ሺህ 241 ተማሪዎቸ‍ን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 377 ተማሪዎችን በሦስተኛ ዲግሪ ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎቹ መካከል 2 ሺህ 646 ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በምርቃት መርሀ ግብሩ እንደተጠቀሰው በቅርቡ በተሰጠው ሀገራዊ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 3 ሺህ 960 ተማሪዎች ውስጥ 91 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን እና በ18 የትምህርት ፕሮግራሞች ደግሞ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፋቸው ተገልጿል።አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 417 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው ለ76ኛው ዙር ያስተማራቸውን 3 ሺህ 542 ተማሪዎቸ‍ን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 2 ሺህ 241 ተማሪዎቸ‍ን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 377 ተማሪዎችን በሦስተኛ ዲግሪ ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎቹ መካከል 2 ሺህ 646 ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በምርቃት መርሀ ግብሩ እንደተጠቀሰው በቅርቡ በተሰጠው ሀገራዊ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 3 ሺህ 960 ተማሪዎች ውስጥ 91 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን እና በ18 የትምህርት ፕሮግራሞች ደግሞ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፋቸው ተገልጿል።

Photos from AAU Fast Information's post 23/01/2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የአቶ አቤ ሳኖን መልዕክት ይዘው የመጡት የማዕከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ እና ከፍተኛ ሀላፊዎች በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በመገኘት ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር ) አስረክበዋል፡፡

አቶ ሙሉነህ በመልዕክታቸው ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት ግንባር ቀድም ተቋም በመሆን ለሀገራችን ዕድገትና ልማት የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት የማይተካ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታውሰው ለመጪው ጊዜም መልካም የስኬት ዘመን እንዲሆን ለዩኒቨርሲቲው ተመኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንትሳሙኤል ክፍሌ (ዶ /ር) በበኩላቸው ለእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው አመስግነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ታላቅነቱ እና አንጋፋነቱ ለተቋማችን የሰጠው ክብር፤ በአርዓያነት የሚወሰድ ሆኖ በመጪው ጊዜም እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ከባንኩ ጋር ያለውን አጋርነት በማጠናከር ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡

19/01/2026

በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ደረጃን የያዘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኪው ኤስ የዓለም ዩኒቨርሲቲ ደረጃዎች መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ደረጃ ይዟል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚያስመዘግቧቸው የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ውጤቶችን በመመዘን የዩኒቨርሲቲ ደረጃዎችን በሚያስቀምጠው QS World University Rankings አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲነት ደረጃን መያዝ ችሏል። የደረጃ…

AAU Fast Information

Want your business to be the top-listed Realtor/realty Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa
1000