SAddis information
I hate fore something.
15/03/2025
አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ!!
በዛሬው ዕለት ወደ አመሻሽ አከባቢ ከመንፈሳዊ ጉዞ እየተመለሱ የነበሩ የሻሸመኔ ወጣቶች "መኪናው ፍሬን በመበጠሱ" ምክንያት በዎላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሳ ወንዝ ተገልብጠው እስካሁን የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉንና ለጊዜው በቁጥር ባልተገለፁት ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ዓመታዊ ንግስ በዓል እየተመለሱ የነበሩ የሻሸመኔ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወጣቶች የመኪና ፍሬን በመበጠሱ በበዴሳ ወንዝ ውስጥ በመገልበጡ 20 ሞት፣ 16 ከባድ ጉዳት፣ 6 ቀላል ጉዳት እና 4 በሰላም የተረፉ ሲሆን ከጉዳቱ ክብደት አንጻር ተጨማሪ ሞት ሊመዘገብ ይችላል ተብሏል።
በድንገተኛ አደጋ ለሞቱት ወገኖቻችን ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!
@ ዎላይታ ታይምስ
15/03/2025
ሔዝቦላህ ስሙ እየገነነ የመጣው በአውሮፓውያኑ በ80ዎቹ ነው ።
በተለይ የሊባኖስን የእርስ በርስ ጦርነትን (1975-1990) ተከትሎ ወታደሮቹ ደቡባዊ ሊባኖስን መቆጣጠራቸው ሰፊ ድጋፍ አስገኝቶለታል።
ባለፈው ጥቅምት የእስራኤል መከላከያ ኃይል 'አልቀርድ አልሐሰን'' (AQAH) የተሰኘውን የብድር እና የቁጠባ ባንክን በቦንብ ሲደበድብ ለብዙዎች ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር።
ይህ የሊባኖስ የብድር እና የቁጠባ ባንክ ውስጥ ውስጡን የሔዝቦላህ ምሥጢራዊ የገንዘብ ዝውውር መሣሪያ መሆኑ በስፋት ይነገራል።
ቡድኑ በዚህ ባንክ ስም ገንዘብ ያስተላልፋል፣ ዶላር ይመነዝራል፣ የገንዘብ ዝውውርን ያሳልጣል በሚል ነው እስራኤል ዒላማ ያደረገችው
https://bbc.in/4i7ufB3
Click here to claim your Sponsored Listing.