Kaffecho
22/04/2026
gallame gaaro tuneba
መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
18/04/2026
ይናገራል መልኩ!
የኦሮምኛ ቋንቋ በሁለት ይከፈላል። አንደኛው ፖለቲካል ኦሮምኛ ነው። ፖለቲካል ኦሮምኛ ያስፈራል። ቆንጨራ የያዙ ወንበዴዎች የሚናገሩት ቋንቋ ነው። ጥሬ ስጋ ቤት G+3 የሚያክል ጫማ አድርገው ቤቱ የጠበባቸው ባለትልቅ ሻኛ ወይፈኖች የሚናገሩት ቋንቋ ነው። ምሽት ክለብ ውስጥ የውስኪ ጠርሙስ "በሽጉጥ ተኩሰን እንከፍታለን" ብለው በሦስት ሚሊዮን ብር የሚወራረዱ ጥጋበኛ ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ ነው። ነፍጠኛ፣ ወራሪ፣ ሰፋሪ የሚሉ ቃላት ከፖለቲካል ኦሮምኛ መዝገብ ቃላት አይጠፉም። እንደ ገላና ያሉ "የሰው ቡሎች" መገለጫው ናቸው። ከዚህኛው ኦሮምኛ ጋር ችግር አለብን።
ሌላኛው ማኅበራዊው ኦሮምኛ ቋንቋ ነው። በዚህ ቋንቋ አበበ አብሹ "ሸጌ ብርቱካኔ ኮ" ብሎ ሲዘፍን ቋንቋው የአፍ መፍቻ ቋንቋህ የሆነ ያክል ይሰማሃል። አሊ ቢራ "ሞናሊዛን" ሲዘፍን አንዲት ቀጭን፣ ፀጉሯ የሚዘናፈል፣ አፈንጫዋ ሰልካካ ሴትን በአዕምሮህ እየሳልክ ምናባዊ ፍቅር ሊይዝህ ይችላል። በዚህኛው ኦሮምኛ ቋንቋ ሐመልማል አባት "ኪያ ኪያ" ስትል ለቋንቋው ቤተኛ የሆንክ ያህል ይሰማሃል። አብተው "ያኒኮ" ብሎ የዘፈነውን ንጉሡ ታምራት ሲደግመው እንደ አዲስ ትሰማዋለህ። አቡሽ ዘለቀ "ጃል ጅሎ" ብሎ ሲዘፍን ጃምቦ ጆቴ "ቤልባ" ብሎ ሲዘፍን ቋንቋው ደስ ይላል። ሀጫሉም እኮ "ኦል ማንኬን" ሲዘፍን ደስ ይለናል። ከዚህኛው ኦሮምኛ ጋር ግንኙነታችን ሠላማዊ ነው።
ቋንቋ እና ሰው አንድ ናቸው። ይመሳሰላሉ። ሰው ከማታውቀው ቋንቋ ጠበኛ ያደርግሃል። ሰው ያንኑ ቋንቋ መልሶ "እንዲህ ደስ ይላል እንዴ?" ያስብልሃል። ቄስ በላይ እና አቡነ ናትናኤል ሲዘምሩበት እንኳን ልዩነት አለው። ቋንቋ ከስብዕና ጋር ጥልቅ ግንኙነት አለው። It is how the speaker behaves!
ስብሃት ነጋ "አማራን እና ኦርቶዶክስን እንዳያንሰራሩ አድርገን አርቀን ቀብረናቸዋል" ብሎ ፖለቲካል ትግርኛን ፈጠረ። ከዚህ ጊዜ ወዲህ ሰለሞን ኃይለ "ልዋመይን" ብሎ የዘፈነበትን ትግርኛ ቋንቋ ስሰማ እና ባለጊዜ እያሉ የሆነ ካኪ ጃኬት የለበሰ ሰው ውልና ማስረጃ ሄዶ "ቧይ አተ ቶሎ በል" እያለ ሲሸልል ራሱ ትግርኛ ቋንቋ ይሸክከኛል።
ቋንቋን ተናጋሪ ያሳምረዋል። ተናጋሪ ያበላሸዋል። ይሄን ገላና ጋሮምሳ የተባለን ንክር ሰውዬ እየው። ፊቱም ንግግሩም "መጣውብህ" የሚል ሰውዬ። ይሄ ሰውዬ የሚዘፍንበት ኦሮምኛ ደስ አይለኝም። ፖለቲካል ኦሮምኛ ነው። ይሄን ሰውዬ ሳይ ጥበብ ሙዚቃዊ ቃና ምናምን ሳይሆን፣ መሃል አስፋልት ላይ ሽጉጥ የሚተኩሱ አንጎል የለሽ ሰዎች ናቸው ወደ አዕምሮዬ የሚመጡት። ምክንያቱም ይናገራል መልኩ!
18/04/2026
#ዜናመሠረት አዲሱን የቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈን ሲያዳምጡ ተገኙ የተባሉ ከመቶ በላይ ወጣቶች አዲስ አበባ ውስጥ መታሰራቸው ተሰማ
ፖሊስ በበኩሉ በዘፈን ሰበብ የፊታችን ግንቦት ወር የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ለማስተጓጎል በማሰብ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ ነበር ብሎ ምላሽ ሰጥቷል
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://www.meseretmedia.org/p/e57
በ30% ቅናሽ የፕሪሚየም አባል ለመሆን ሊንኩን ይከተሉ:
https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
አዲሱን የቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈን ሲያዳምጡ ተገኙ የተባሉ ከመቶ በላይ ወጣቶች አዲስ አበባ ውስጥ መታሰራቸው ተሰማ (መሠረት ሚድያ)- የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ዘፈን መውጣቱን ተከትሎ ከሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ባደረጉት አሰሳ የፊታችን ግንቦት ወር የሚ...
08/04/2026
ወጣት በጎሪጥ ተመልካቹ በወጣት የሚመራው የቦንጋ ከተማ አስተዳደር፤ አምባሰደሩን ወጣት መደገፍ ግዴታው ነው
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር በወጣት ይመራል። በትምህርት የበቃም መሪ እንዳለው ሰምተናል። መሪነትን ሲናገሩም በተደጋጋሚ አይተናል። "መሪነት ይህ ነው ይኸኛው አይደለም" ሲሉም እስኪደክመን ንግግራቸውን ኮምኩመናል።
ይሁንና "ከበሮ በሰው እጅ" የሆነበት የመዋቅሩ አመራር ወጣቶችን በጎሪት የሚመለከት፤ የተቀመጠለት ሀላፊነት መጎብኘት እና በየመድረኩ መታየት የሚመስለው ሆኖ አይተናል።
ህልመኛ ወጣቶችን መደገፍ፤ ለአከባቢያቸው አምባሳደር የሆኑትን ማበረታታት የሥራቸው አካል መሆኑን አስታዋሽ የሚሹ ይመስለኛል እና አስታውሷቸው።
በህዝብ ይሁንታ በህዝብ ሀብት ህዝብን ማገልገል ግዴታቸውም እንደሆነ ነጋሪ ያሻቸዋልና "ሁሉን አውቃለሁ" ይሉም ይሆናልና ደጋግማችሁ አስረዷቸው።
የቦንጋን ታሪክ መናገር ብቻ ሳይሆን ቦንጋን ዳግሞ በብዙሃን እንድትጠራ ያደረገውን ወጣት ስፖርተኛ ባይተዋር አታድርጉት፤ ከፍ ብላችሁ ካላችሁበት ወደ ህዝብ በመውረድ የጊዜውን የአመራር ተግባር ፈፅሙ።
ዶች ኤችዲ
በአንድ ቡጢ እጥልሃለሁ 🔥- ንቃተ ህሊና
ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ለሚደረገው በታሪክ የመጀመሪያው የ "MMA" ፍልሚያ ሁለቱ ስፖርተኞች እያደርጉት ከነበረው ዝግጅት በኋላ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።
ዘለፋ፣ ቡጢና ትግል በበዛበት በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የስፖርቱ ቤተሰብ፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የሁለቱ ስፖርተኞች አድናቂዎች ተገኝተው ታድመውታል።
"ንቃተ ህሊና" በጆኒ በጥፊ መመታቱን ተከትሎ ለመልስ ምት ያደረገው ትግል የሁነቱ አካል ሲሆን በዚያ ያሉ ሰዎችም አንዱ እንዲመታ ከፈቀዱ በኋላ ሌላኛውን ጠፍረው የያዙበት አጋጣሚ ለትዝብት የሚዳርግ ሆኗል።
የከተሜነት አክራሪዎች የክፍለ ሃገር ተወላጆችን ለማንኳሰስ እና ለማሳነስ የሚያደርጉት የሁል ጊዜ የንቀት ቃላትን እንደ ሁል ጊዜው በተደጋጋሚ ለሚጥለው ጆኒ፤ በንቃተ ህሊና በኩል "የመጣውት አዎ ከጫካ ነው። የመጣሁበት የምሄድበትንና የምደርስበትን አይወስንም። በመጣውበትም የምኮራ ነኝ። ያን ቀን ደግሞ አሳይሃለሁ" የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።
በጆኒ በኩል ያሉ የአከባቢ እና የትውልድ ቀዬ የሚያብጠለጥሉ ቃላት የሁልጊዜ ልምምዶች መሆናቸው ግን የተክለ ሰውነት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትና ብስለት ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ማሳያ ሆኗል።
እንቁራሪትዋ አፍልታለች ትረጋጋለች
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
1000