Mesi ye abi

Mesi ye abi

Share

07/06/2026

▫️የሰው ክፉ አለ !

አንተ ከራስህ ቀንሰህ ጥሩ ነገር ስታደርግለት እሱ ግን በአንተ ላይ ክፉ የሚመኝ ፤ ልታግዘው ስትፈልግ አንተን ጥሎህ ለመሄድ የሚሞክር ፤ በከፍታው ስትደግፈው መውደቂያህን የሚያመቻችልህ ክፉ ሰው አለ።

በዚህ ሰዓት አንተ የሰውን በጎ ጎን ብቻ ለመመልከት ስትሞክር፣ እናትህ ግን ከጀርባው ያለውን ተንኮል ታያለች። እሷ መጥፎ ነገርን የምታሳይህ ህይወትን ስለምታውቃትና ካንተ በላይ ሰውን ስላጠናች እንጂ እንደአንተ ቀና ስላልሆነች አይደለም።

ለፍተህ ያገኘኸውን ጊዜህን እና ጉልበትህን ለማይገባው ሰው አትስጥ።

ከመጎዳትህ በፊት አስቀድመህ ተከላከል ፤ የእናትህን ምክር ስማ።

መልካም ቀን 🙏

19/06/2024

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዘመናዊ ዲጂታል ብሬሎችን ተረከበ።
***
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኮሪያው ሴሎም ኢንተርናሽናል
ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ጋር ከዚህ ቀደም ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ነው እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዲጂታል ብሬሎችን የተረከበው። በቀጣይ ደግሞ ተመሳሳይ ቀሪ 30 ብሬሎችን በድጋፍ የሚረከብ ይሆናል።

ይህ ዘመናዊ መሳሪያ ማየት የተሳናቸው የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከወረቀት ብሬል ተላቀው በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚረዳ ሲሆን፤ ከተለያዩ ዳታቤዞችም ጥናታዊ ጽሑፎችን ያለምንም ክፍያ አውረደው መጠቀም ያስችላቸዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ለዲጂታላይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ ይህ ልዩ ድጋፍም የትግበራው አንዱ ማሳያ ነው።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa