Great silte
17/12/2023
02/09/2023
ግልጽና አጭር መልዕክት ለፌደራሉ መጅሊስ አዲስ አበባ
ለሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሶ ትምህርት መማር ክልክል ነው የሚል ግልጽ ሃገር አቀፍ አዋጅ በሌለበትና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ኒቃብ አድርገው እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ባለበት ተጨባጭ ላይ…የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊም ጠሎች ግን የግል ጥላቻቸውን ተቋማዊ በማድረግ የበርካታ ሙስሊም የእህቶቻችንን ህገ መንግስታዊና ሰብዓዊ መብት በማን አለብኝነት ስሜት እየጣሱ ይገኛሉ !!
ይህም አሳዛኝ ግፍና ጥቃት ከአካባቢው የሙስሊም ተወካዮችና ማህበረሰብ አቅም በላይ መሆኑም ተደጋግሞ ታይቷል !!
በመሆኑን ይህን መሰሉ የጉንችሬ ከተማ የሙስሊም ጠሎች አስነዋሪ ተግባርና ድርጊት በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የተቃጣና የተፈጸመ በደል መሆኑን የፌደራል መጅሊሡ ግንዛቤ ወስዶ እንደ አንድ ግዙፍ ማህበረሰብ ተወካይነቱ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደልና ግፍ ለሚመለከታቸው ተቋማት በማሳወቅና ብርቱ ክትትል በማድረግ ከዚህ በተጨማሪም በተቋሙ የህግ ክፍል አስቸኳይ የህግ ተጠየቅ እንቅስቃሴን በማስጀመር ህጋዊ መብትን የማስከበር እርምጃ ይወሰድ ዘንድና በየግዜው የተሄደበትን አቅጣጫና የተገኘውን ምላሽ በይፋዊ መግለጫ ያሳውቅ ዘንድ አጥብቀን እንጠይቃለን !!
___________________________
17/08/2023
አልሀምዱሊላህ!
በጠሮ መስጂድ ጉዳይ ታስረው የነበሩ አባቶች መፈታታቸው ተገለፀ።
…
ሃሩን ሚድያ ነሀሴ10/2015
…
በጠሮ መስጂድ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሀሰት ታስረው
በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ይገኙ የነበሩ ሁሉም አባቶች ከእስር ተፈተው አ.አ ገብተው ከቤተሰብ ጋር ተቀላቅለዋል።
…
ሃሩን ሚድያ በቅርቡ የጠሮ መስጂድ ጉዳይን አስመልክቶ የሚመለከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዋች አናግሮ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል የአዲስ አበባ መጅሊስም የጠሮ መስጂድ የተፈጠረውን ያለመግባባት በቅርቡ እንደሚፈታ የአዲስ አበባ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ሼህ ሁሴን በሽር ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።
…
©ሃሩን ሚድያ
Click here to claim your Sponsored Listing.