Sello Media
28/05/2026
!
በፖለቲካ መድረክ ላይ ትልቁና የመጨረሻው ዳኛ ሕዝብ ነው። ሕዝብ ደግሞ የሚሰጠውን ፍርድ በምሬት ወይም በጩኸት ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ካርዱና ለልማት በሚያሳየው ዝግጁነት ይገልጻል።
ቁሕዴፓ አመራሮች በአዲስ አበባ መግለጫ አውጥተው የፈጠሩት ሁካታ ካለፈው የታሪክ ስህተት ያልተማረና የቁጫን ሕዝብ ንቃተ-ሕሊና የናቀ የከሰረ ፖለቲካ ማሳያ ነው።
ቁሕዴፓ በቁጫ አካባቢ በሕዝብ ዘንድ ሙሉ በሙሉ መተፋቱንና የመደገፊያ መሬት ማጣቱን በሚገባ ያውቀዋል። ለአመታት የሕዝብን ስሜት በመኮርኮርና በማንነት ስም በመነገድ የቆየው የፖለቲካ ቁማር ማብቂያው ላይ ደርሷል።
ፓርቲው በምርጫ ሜዳው ላይ ወርዶ መወዳደርና ማሸነፍ እንደማይችል ሲረዳ መሸነፉን አስቀድሞ በማረጋገጡ ገና ምርጫው ሳይካሄድ የሽንፈት ማስተባበያ ሰበብ ማዘጋጀት ጀምሯል።
የሕግ አንቀጾችን መጥቀስና ተገለልን ማለት ሕዝባዊ መሠረት ማጣትን ለመሸፈን የተዘረጋ የሽንፈት መጋረጃ ነው።
የቁጫ ሕዝብ ዛሬ የትናንቱን የውዥንብር ፖለቲካ ወደ ኋላ ጥሏል። በአካባቢው ለብልጽግና ፓርቲ የወጣውና የታየው ተዓምራዊ የሕዝብ ማዕበል የሚያረጋግጠው አንድ እውነት አለ። ሕዝቡ የሚፈልገው ጩኸት ሳይሆን ልማት፣ ሁከት ሳይሆን ሰላም፣ መገለልን ሳይሆን አብሮነትን ነው።
ያ የታምር ሰልፍ ለቁሕዴፓ አመራሮች የፖለቲካ ሞት የዕርድ አዋጅ ነበር። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ለብልጽግና ያለውን ታማኝነትና ድጋፍ ሲያሳይ፣ ተቃዋሚዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ጨለማ መሆኑን ተረዱ።
ከዚህ ማዕበል ማምለጥ እንደማይችሉ ሲያውቁም ምርጫው እንዲራዘም ወይም እንዲሰረዝ መጮኽን እንደ ብቸኛ አማራጭ ወሰዱት።
እውነተኛ የሐሳብ ልዕልና ያለው ፓርቲ የሕዝብን ድምፅ አይፈራም ምርጫ እንዲራዘምም አይማጸንም። የቁሕዴፓ ጩኸት የጥንካሬ ሳይሆን የከፍተኛ ፍርሃት መግለጫ ነው። መሸነፍን በፀጋ መቀበል ያቃተው ፖለቲካ፣ ተቋማትንና ሥርዓቱን በመወንጀል የራሱን ውድቀት ለማስታገስ ይሞክራል።
የሕዝብን ልብ ማሸነፍ አቅቶት፣ በምርጫ ሳጥን ውስጥ የሚጠብቀውን ውርደት በመፍራት አዲስ አበባ መሽጎ የሽንፈት መግለጫ የሚያረቅ የከሰረ ኃይል አለ።
የቁጫ ሕዝብ ወደ ኋላ አይመለስም ድምፁንና ውሳኔውን በተግባር አሳይቷል። የቁሕዴፓ ጩኸትም ቀድሞ የተረጋገጠ ሽንፈትን በጩኸት ለመቀየር የሚደረግ የሰነፎች የመጨረሻ ትግል ብቻ ነው።
27/05/2026
04/05/2026
ጋሞን ማከፋፈል ዓላማው ያደረገ ነውረኛ ፓርቲ
ህጋዊ እውቅና በሌለው መዋቅር ስም ቅስቀሳ ማድረግ ህገወጥ ተግባር ነው። አንድ የፓርቲ እጩና የህግ ባለሙያ ነኝ ከሚል አካል የማይጠበቅ አሳፋሪ የወንጀል ተግባር!
አቶ ቡንካሾ ሀንጌ በራሱ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ህጋዊ መሰረት እና እውቅና በሌለው ወረዳ
"ጋሞ ዞን ካምባ ምርጫ ክልል ባልታ ዙሪያ ወረዳ ቦኮ ቀበሌ" በማለት ያጋራው ሀሰተኛ መረጃ ህዝቡን አስቆጥቷል።
ለምርጫ ቅስቀሳ የ“ሕጋዊ መዋቅር” (የተመዘገበ ፓርቲ፣ እጩ ወይም የተፈቀደ ዘመቻ) ማድረግ ብቻ ይፈቀዳል። የሌለ መዋቅር ብሎ መጠራት እና በዚህ ስም መቀስቀስ ህገወጥ ተግባር ብቻ ሳይሆን አደገኛ ወንጀልም ነው፤ ህዝብን ማከፋፈልም ጭምር።
አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ነኝ የሚል አካል አጠቃላይ የፖለቲካ አስተያየት መግለጽ፣ ፖሊሲ ላይ መከራከር፣ ዜጎችን ያንን ፓርቲ እንዲመርጡ ማበረታታት (voter education) ከማድረግ አልፎ ሐሰት መረጃ መስጠት በህግ የምያስጠይቅ ወንጀል ነው።
ሀሳብ መሸጥ እንጅ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት አይፈቀድም። ፖለቲካ ግቡ የጋራ የሆነ ዓላማን ማስፈፀሚያ መሳሪያ ነው። ጋዴፓ ጅምር አካባቢ የምስረታ ዓሃማው ይኼ ልሆን ይችል ነበር፤ በስተመጨረሻም ዓላማውን ከሳተው ፓርቲ ሰዎች ከወጡ በኋላ ደጋፊ ያጡ እነቡንካሾ አይነቶች በሀሰተኛ መረጃ ህዝብን ማደናገር ጀምረዋል።
ዛሬ ላይ ከፓርቲ ቁመና ይልቅ የጩኸት ማስተጋቢያ አምፕልፋየር የሆነው ቡድን በምርጫ ቦርድ ያልተመዘገበን ድርጅት "ሰላም-ጋዴፓ" በሚል ስያሜ ማንቀሳቀስ የህዝብን አመኔታ ከማሳጣቱም በላይ የፖለቲካ ግልጽነትን የሚያጎድል ተግባር ነው፤ በመሆኑም ተለዋዋጭና አሳሳች ስሞችን ከመጠቀም ይልቅ እንደ "ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት" ግልጽ የሆኑ መጠሪያዎችን መጠቀም ይገባል።
ማደናገርን አስወግዶ በህጋዊ መንገድ መንቀሳቀስ ለሀገር ሰላምና መሰረታዊ በመሆኑ፣ ተዓማኒነት ያለው የለውጥ ጉልበት ለመፍጠር ከስሜታዊነት በጸዳ መልኩ ራስን በግልጽ ማስተዋወቅና ለህግ ተገዢ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
በተለይ አሁን ላይ የፓርቲው ህልውና የተሰኙ አንደበተ ቁልፍ ሰዎች የሚያደርጉት ተግባር ሌላ ነው። ድርጅቱን ስሙንና ግቡን ሳይቀይሩ ጯሂ የሚዲያ ተቋም አድርገውታል። ይህ ስስ በሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለተቀባይነት እና ለዝና የሚያመቻምች ስራ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ግን እስከመቼ ?
ህዝብ ይሰለቻል መበጥበጥንም አይፈልግም። ጋዴፓ ከዛሬ 7 ዓመት በፊት መስራቾቹ ጭምር የተውት ፓርቲ ሆኗል።
ድምፃቸው ገደል ማሚቱ ሆኖ የሚሰማቸው የወሬ ስንቆች አሉ። ተው እንበላቸው ።
03/05/2026
በጋሞ ዞን፣ ገረሴ-ቦንኬ ምርጫ ክልል የሠላም ጥምረት ፓርቲ ዕጩ የሆኑት ቡንካሾ ሀንጌ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን (NEBE) መመሪያዎች በግልጽ በመጣስ ትናንት በቦንኬ ጮሻ ገበያ ሕገ-ወጥ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል።
በገበያ ስፍራዎች፣ በንግድ ማዕከላትና በህዝብ መገልገያዎች ውስጥ የፖለቲካ ቅስቀሳ ማድረግ በምርጫ ህጉ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ እየታወቀ፤ ፓርቲው ህግን በገሃድ መጣሱ የዴሞክራሲያዊ ምርጫን መሰረት የሚንድ እና የህግ የበላይነትን የሚፈታተን ድርጊት ነው። ፍትሐዊና ተዓማኒ ምርጫ ሊረጋገጥ የሚችለው ሁሉም ተወዳዳሪዎች ያለምንም ልዩነት ለሕግና ለሥነ-ምግባር ደንቦች ተገዥ ሲሆኑ ብቻ ነው!
ስለሆነም፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት በዚህ የህግ ጥሰት ላይ አፋጣኝና አስተማሪ የሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ (ከማስጠንቀቂያ እስከ ቅስቀሳ ማገድ) በመውሰድ፤ የምርጫው ሂደት ፍትሐዊና ህጋዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጡ አበክረን እንጠይቃለን።
#ምርጫ
Click here to claim your Sponsored Listing.