Al-Afia
Dry Mouth ( Xerostomia)
የአፍ መድረቅ ችግሮች ምክንያቶችና መፍትሄዎቻችው
የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ (saliva) አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።
ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባስቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚራዳ ሁኔታን ይስመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናድርግና ልምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኤንዛየምስ የማመንጨት ተግባርን ይስከናውናል።
የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊይስቃውስ ይችላል።
የአፍ መድረቅ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
* አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን
*መጥፎ የአፍ ጠረን
*ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር
*የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት
*የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።
የአፍ መድረቅ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
የአፍ መድረቅ የሚመጣው አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።
* መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንየሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።
*እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።
*የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።
*ሲጋራ ማጤስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።
*ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።
*ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን ይስሉ ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
*ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።
ከአፍ መድረቅ ጋር በተያያዘ የሚመጡ ሌሎች ችግሮች ምንድን ናቸው?
* የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
*የከንፈር ቁስለት
*የፈንገስ ኢንፌክሽን
*የከንፈር መሰነጣጠቅ
*የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።
አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ መድሀኒት እንዲውስዱ ይደረጋል።
የአፍ መድረቅ እንዲቀንስልን በቤት ውስጥ ልንጠቀማቸው የምንችላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
*ውሀን ይጎንጩ ውሀን መጎንጨት የዘወትር ልማር ማድረግ፣ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ ለማላመጥ እና ለመዋጥ እንዳይችሉ በውሃ ማወራረድ።
*በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ የማንኮራፋት ችግር ካለብዎና ሌሊት አፍዎን ገጥመው መተኛት ካልቻሉ ለማንኮራፋቱ ሀኪምን ያማክሩ።
*ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካ ወይንም ከረሜላ መጠቀም
*ከንፈርዎን ቫዝሊን ወይንም የከንፈር ቅባት በመቀባት ያለስለሱ።
ምች የሚባል በሽታ ግን ምንድነው ?
( ምች በፀሐይ ይመጣል ወይስ አይመጣም?)
🔘 ምች የሚባለው በሽታ በእንግሊዘኛው herpes labialis የሚባለው ሲሆን ዋናው የበሽታው ምልክት ደሞ ሄድ መጣ የሚሉ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስሎች ናቸዉ።
የምች መንስኤው ምንድነው?
የበሽታው ዋናው መንስኤው herpes simplex የሚባለው ቫይረስ ሲሆን በመሳሳም ወይም በ ሌሎች አካላዊ ግንኙነቶች አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ::
ምልክቶቹ
- የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት
- ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች
- ትኩሳት
-የራስ ምታት
- የጡንቻ ላይ ህመም
-የአንገት ላይ ንፍፊትቶች እብጠት
-ለምች የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው?
1. ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ
ፀሐይ ብርሃን ለብቻው ምች አያመጣም።
ነገር ግን ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex 1) ቀድሞ ይዞን እራሱ ነርቭ ህዋሶች ዉስጥ ይደብቃል ።
የፀሐይ ብርሃን ዉስጥ ባለው ultraviolet የሚባለው ጨረር ደሞ ሊነሳሳው (re activate ሊያረገው) እና ከተደበቀበት የነርቭ ስር ዉስጥ በ መውጣት ድጋሚ ወደ ቆዳ አካባቢ በመሄድ ሄድ መለስ የሚል ቁስል ሊያመጣ ይችላልይችላል
2. ቅባት ያለዉ ምግብ መመገብ
3. ጭንቀት
4. ኤች አይ ቪ ኤድስ
5. የካንሰር ህክምና
6. የወር አበባ ዑደት ጊዜ የሆርሞን መለዋወጥ
የጤና ባለሙያ ማማከር ያለብን መቼ ነው ?
- የበሽታ መከላከል ብቃት መቀነስ/የተዳከመ ከሆነ
- ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
- የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
- ህመሙ በተደጋጋሚ ከተከሰተ
-በአይን የመቆጥቆጥ ስሜት ሲሰማ
ሕክምናውስ ምንድን ነው?
-ጸረ- ቫይረስ መድሃኒት እና የህመም ማስታገሻ መድሐኒት መዉሰድ
- በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን
-በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ
- የአእምሮ ዉጥረትን/ ጭንቀትን መቅነስ
- ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ተክል ቅጠል በማሸት ቁስሉ ላይ ማድረግ/መቀባት
-ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል፤
- ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ስለሆነ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ :- በተለይ አይንንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ፤
- የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
-የእጅን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካት በፊት እጅዎን በደንብ ይታጠቡ ።
ሕጻናት ድንገተኛ የነስር ሕመም ሲያጋጥማቸው ማድረግ የሚገባዎ 7 ነገሮች
• ነስርን ብዙ ጊዜ ቤት ዉስጥ በቀላል ዘዴዎች ማቆም ይቻላል፡፡ ወላጆች ግን መረጋጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡የልጅዎን ጭንቀላቱን ትንሽ ወደ ፊት ዘንበል አርጎ አፍንጫው አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የ አፍንጫ ክፍል ቢያንስ ለ10 ደቂቃ ጫን አርጎ መያዝ :: ቶሎ ከለቀቁ መልሶ ሊደማ ይችላል፡፡
• በዚህ መንገድ ቀላል ነስር ከሆነ ይቆማል፡፡ ካልተሳካ ግን ለተጨማሪ 10 ደቂቃ አሁንም ደግሞ አፍንጫውን ጫን አርጎ መያዝ ይገባል፡፡
• በነዚህ ሁለት ሙከራዎች ወይም በ 20 ደቂቃ ዉስጥ ካልቆመ በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ልጅዎን ሐኪም ዘንድ
• በዚህ ወቅት ልጆዎ በአፉ እንዲተነፍስ ይንገሩት፡፡
• ይጠንቀቁ!በፍፁም ልጆዎን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ወይም ማንጋጠጥ የለበትም:: ምክንያቱም ቀና ስላለ ደሙ ወደ ውጭ አይፍሰስ እንጂ ወደ ዉስጥ በምግብ ቱቦ በኩል በብዛት እንዲፈስ እና ወደ ጨጓራው እንዲገባ ያረጋል ይሄ ደሞ ከፍተኛ የደም ማነስ እና ትውከት ሊያስከስት ይችላል::
• ሶፍት ወይም ሌላ ነገር ወደ አፍንጫ አይክተቱ! ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መድማቱን ሊጨምሩት ይችላሉ፡፡
• የልጅዎን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉ፡፡ነስሩ ከቆመ በዋላ ለተወሰነ ሰዓት ልጆ አፍንጫውን እንዳይነካካ እና በኃይል እንዳይናፍጥ ከባድ ነገር እንዳያነሳ ያርጉት
የልጆች ነስርን መከላከል ይቻላል ?
አዎ መከላከል ይቻላል፡፡ ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ግን የሚቻለው በሐኪም ሲታከም ነው::
መከላከያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
ልጆች አፍንጫቸውን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ነገሮች ማራቅ
አፍንጫቸውን እንዳይነካኩ ማስተማር
የልጆች ጥፍርን ማሳጠር
የአየር ንብረቱ ደረቅ ከሆነ አፍንጫቸው ዉስጡን ቫዝሊን በመጠኑ መቀባት ወይም እንፋሎት መታጠን
ጉንፋን እና አለርጂን በአግባቡ መታከም
መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትእዛዝ አለመውሰድ
ቋሚ የህፃናት ሕክምና ክትትል ማድረግ
በነስር ሕመም የታመመ ልጅዎን መቼ ነው ሆስፒታል መውሰድ የሚገባዎ?
ከላይ እንደ እንደተጠቀሰዉ የማይቆም ከሆነ
ባንዴ ብዙ ደም መፍሰስ ካለ(ከ1 ስኒ በላይ)
ልጆዎ ራስ ማዞር እና መሳት ካጋጠመው
ተደጋጋሚ ነስር እና የጥርስ መድማት ካለ
ቆዳው በቀላል ምት(አደጋ) የሚበልዝ ከሆነ
ከ 2 ዓመት በታች ነስር ከተከሰተ
ልጆዎ ከዚህ በፊት የደም ማነስ ካለበት
ተከታታይ ደም የቀላቀለ ትውከት ካለ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Addis Ababa