Sky Ethiopia

Sky Ethiopia

Share

28/06/2026

"በጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ ካቢኔ ውስጥ ሁለት ሚኒስትሮች ሃይማኖት የላቸውም" ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር)

የቀድሞ የብልፅግና ፓርቲ ሹም የነበሩት ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር) ከሰመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉት ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር) ከኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ከገለፁ በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ከዕይታ ጠፍተው ነበር።

ይሁን እንጂ በፌስ ቡክ ገፃቸው መንግሥትን ጠንከር ባሉ ቃላት በመተቸት እና በመውቀስ ሃሳቦቻቸውን ማጋራታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋ ሆድ እና ጀርባ እንደሆኑ ማሳያ ተደርጎ ሲነገር መቆየቱ ይታወሳል።

ዮናስ ዘውዴ(ዶ/ር) በአሁን ወቅት ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን አስታውቀዋል። በአሜሪካ አትላንታ "ስመጥር በሆነ ዩኒቨርስቲ ውስጥ" ትምሕርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዮናስ በሰጡት ቃለመጠይቅ ምን ተናገሩ?

👉 የብልፅግና ፓርቲን ስያሜ ያወጡት የቀድሞ ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ብናልፍ አንዷለም መሆናቸውን ገልፀዋል።

ለፓርቲው ስም ለማውጣት በአዳማ በተካሔደ ውይይት ለፓርቲው "ጤፍእና ቡና"የተሰኘ አማራጭ ስያሜ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል።

👉በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ካቢኔ ውስጥ ሁለት ሚኒስትሮች ሃይማኖት የላቸውም ብለዋል። በስም ያልጠቀሷቸው እነዚህ ሁለት ሚኒስትሮች ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት እንደሚያውቋቸው ገልፀው፤ "ራሳቸውን ከኦርቶዶክስ ጋ ሊያመሳስሉ ይችላሉ [እንጂ] ጴንጤ ወይ ሙስሊም እንዳልሆኑ አውቃለሁ" ብለዋል።

👉በካቢኔው ውስጥ "የኦርቶዶክስ ቁጥር በጣም አናሳ መሆኑን አውቃለሁ" ብለዋል። አክለውም "ለምን እንደዚህ እንዲደረግ ተፈለገ?" የሚለውን ግን እንደማያውቁ ነው ያስረዱት።

ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር) ዝርዝር ገለፃ ባይሰጡም ከ ኃላፊነት የለቀቁት ልክ እንደ ለማ መገርሳ "የማልስማማባቸው ጉዳዮች ስላሉ ነው ጥዬ የወጣሁት ብለዋል።

12/06/2026

Maadriid Barnaardoo Siilvaa mallatteessifachuuf waliigaleera

Harka Baarseloonaafi Atileetikoo Maadiriidii baafateera

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
Addis Ababa
1000