Mercy Reformed Church

Mercy Reformed  Church

Share

Telegram: Contact @savingWord 11/03/2024

Sermon audio of Mercy Reformed Church telegram Channal

Telegram: Contact @savingWord

26/02/2024

ቅድስና (scancitification) . . . መግቢያ

በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል ፡፡ 1ዮሐ 2፡6

አግዚአብሔር አብ ማን እንደሆነ እና ለኛ ያለው ፈቃዱ ምን እንደሚመስል ያሳየበት ትልቁ መገለጥ እንዲሁም የቅድስናችን ትልቁ ማሳያ እና ምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ኢየሱስ ማንም ያላየውን እግዚአብሔርን የገለጠ የእግዚአብሔር የመልኩ ማሳያ (ምሳሌ) ነው (ዮሐ 1፡18 ፤ 14፡9)፡፡ ያደረገውን ሁሉ ዱካውን እየተከተልን እንድናደርግ በምድር ላይ ምሳሌውን ትቶልን አልፏል (ዮሐ 13፡15 ፤ ማቴ 10 ፡44፤45 ፤ 1ጴጥ 2፡21 ፤ ፊል 2፡5)፡፡

ለመሆኑ ለምንድን ነው ክስቲያኖች ክርስቶስን እየመሰሉ መኖር ያለባቸው ? ለራሳቸው ሲሉ ነው ፡፡ ከኃጢአት በሽታ እና ውጤት መፈወስ እና መዳን ከፈለጉ እርሱ እንደተመላለሰ ሊመላለሱ ይገባል ፡፡ አኛ ክርስቲያኖች አዲስ ፍጥረት ነን ፡፡ አዲሱ ተፈጥሯችን ደግሞ የእግዚአብሔርን እውቀት ፤ ጽድቅ እና ቅድስና ለመያዝ የተፈጠረ ነው (ኤፌ 4፡24 ፤ ቆላ 3፡10) ፡፡ እግዚአብሔርን ሳይመስሉ (በቅድስና ፍጹም ሳይሆኑ) ደህንነትን አግቻለሁ ብሎ ነገር የለም ፡፡ እግዚአብሔር አብ ዓለም ሳይፈጠር የወሰነው የደህንነት ግብ የልጁን መልክ በመምሰል እንድንለወጥ ክርስቶስም በወንድሞቹ መካከል በኩር ይሆን ዘንድ ነው (ሮሜ 8፡29 ፤ ኤፌ 1፡4) ፡፡

ደህንነታችን እሱን ከመምሰል ጋ የተያያዘበት ምክንያት ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ እግዚአብሔርን ከመምሰል ያነሰ ሕይወት በመምራት የማንነት ቀውስ፤ አጠቃላይ ውድቀት ፤የኃጢአት በሽታ እና የኃጢአት ውጤት እና ቅጣት ውስጥ ይገባል እንጂ ደህንነትን አገኘ ሊባል አይችልም ፡፡ ስለሆነም ደህንነታችን ግቡን የሚመታው እግዚአብሔር ያቀደው ሲከናወን ብቻ ነው ፡፡ታዲያ እግዚአብሔር የጀመረውን የቅድስና ስራ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ሩጫ የራሱን ጨርሶ እኛ ድርሻችንን በመፈጸም የዘላለም ሀሳቡን ተጋግዘን እንድናከናውን “ፈረሱም ያው ሜዳውም ያው ብሎ እየጠበቀ ነውን” ? በፍፁም ፡፡ ለኛ የተተወ አንድም ነገር የለም ፡፡ በእኛ የጀመረውን መልካሙን ስራ እንደጀመረው ሁሉ የሚያጠናቅቀውም ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው (ፊልጵ 1፡6) ፡፡ ታዲያ ለምን እንደሱ ተመላለሱ ይላል ? በተጨማሪም አንደ 2 ጢሞ 2፡21 . . . ራሱን ቢያነጻ ፤ 2ጴጥ 3፡18 . . . በእውቀት እደጉ ፤ 2 ቆሮ 7፡1 . . . ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ፤ ማቴ 5፡48 . . . አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ ፍጹማን ሁኑ ፤ ፊል 2፡12. . . የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ ። የሚሉ ትእዛዛዊ መልክቶችን ያስቀመጠልን ለምንድን ነው ? ይሄን ለመረዳት ቅድስና ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ መረዳት እጅግ ወሳኝ ነው ፡፡

የተወደዳችሁ . . በሚቀጥለው ጌታ ቢፈቅድ ቀጣይ ሃሳቡን እንመለከታለን ፡፡

03/05/2023
12/03/2023

በመከራ ውሰጥ ያለ ልበ ሙሉነት ( መዘ 102፡ 1-14 )

አንተ ግን አቤቱ ለዘላለም ትኖራለህ ፡ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው ፡፡ አንተ ተነስ ጽዮንንም ይቅር በላት ፤ የምህረትዋ ጊዜ ነውና ዘመንዋ ደርሷልና ፤

መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ድነታችን በገዛ ራሰችን እምነት ላይ እንጂ ሌላ ሰው ስለኛ ባመነልን መሰረት ላይ ሊገኝ እንደማይችል ይነግረናል ፡፡ አውነት ነው በዚህ ጉዳይ ላይ እያንዳንዳችን ተነጥለን (ራሳችንን ችለን) የቆምን እና የምናደርገው ጥሩም ይሁን መጥፎ ውሳኔ ከራሳችን ጋ ብቻ የተያያዘ ነው ፡፡ ሌላውን ሊጠቅምም ሆነ ሊጎዳ አይችልም ፡፡ ከዚህ ውጭ ባለ ጉዳይ ግን ነገሩ ሌላ ነው ፡፡

ይህን ለመረዳት የእሰራኤልን ታሪክ ማጤን ጥሩ ነው ፡፡ በእስራኤል የበረከት እና የብልጽግና ጊዜ በእስራኤል የሚኖር ሰው ሁሉ የበረከቱ ተካፋይ ይሆናል ፡፡ ምንም እነኳን በግሉ እግዚአብሔርን የማይፈራ እርኩሰ ሰው በመካከላቸው ቢኖርም ለጻድቃን የመጣ ለሱም ይተርፍለታል ፡፡ ለምሳሌ ፡- የህዝቅያስ ታማኝነት ሰናክሬብ አገርን እየወረረ ባለበት ዘመን እስራኤላውያን ከአሶራውያን እንዲጠበቁ ምክንያት ሆኗል (ኢሳ 36 እና 37) ፡፡ በአብዛኞቹም የእስራኤላውያን ኃጢአት ምክንያት በነፍስ ወከፍ ለያንዳንዱ ፍዳ ይመጣ ነበር ፡፡የንስሀ ልብ በሌላቸው ብዙ ሰዎች አማካይነት እግዚአብሔር ህዝቡን ለስደት ሲዳርግ ታማኞቹ እንደ ኤረምያስ እና ሕዝቅኤል አይነቶቹም አብረው የመሰደድ እጣ ፈንታን ደርሶባቸው ነበር (2 ነገ 25 ፤ ኤር 43 ፡ 1-7 ፤ ህዝ 1፡1) ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ባህሪ ነው (ዘጸ 34 ፡ 7)

በመዝ 102 ላይ ባለው የኃዘን እንጉርጉሮ የጸሃፊው ማንነት ባይታወቅም በስደት ወቀት የተጻፈ እንደሆነ ይታመናል ፡፡ ቁጥር 4 ፤ 5 እና 9 በስደቱ ወቅት የነበረውን የመጀመሪያዎችን አሳዛኝ እና ታላቅ የመከራ እና የድህነት ጊዜያቶች በአይምሯችን እንዲሳሉ ያደረጋል ፡፡

ቁጥ 4 . . . እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሰፍሁ ልቤም እንደሳር ደረቀ ፡፡

ቁጥ 5. . . . ከጩኃኸቴ ድምጽ የተነሳ አጥንቶቼ ከስጋዬ ጋር ተጣበቁ ፡፡

ቁጥ 9 . . . አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁና . . . .

ምንም እንኳን ይህ ዘማሪ ቁጥ 10 ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ በመገንዘብ ቢናገርም ፤. . . ከቁጣህ እና ከመዓትህም የተነሳ አንስተኸኛልና ጥለኸኛልምና ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው ግላዊ የኃጢአት ኑዛዜ ግን የለም ፡፡ ይህም ምንም እነኳን እሱ በግሉ እግዚአብሔር የሰጠውን መሬት እና መልካም ትሩፋቶቹን ሁሉ ሊያጣ የማይገባው ታማኝ እስራኤላዊ ቢሆንም ፤ ስደቱ ግን እንደ አገር የሚገባቸው እነደሆነ የሚያሳይ ይመስላል፡፡

ታዲያ በሌሎች የህይወት ውሳኔ እና ምልልስ ሳቢያ የእምነት ሰው መከራ ውስጥ ሲገባ ምን ያደርጋል ? እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ያስባል ፡፡ የዚህ ዝማሬ ጸሃፊ የእግዚአብሄር ተስፋ ስጦታ የህይወት ተኃድሶ እንዳለው ያምናል ፡፡ ስለሆነም በመልካሙ ጊዜ በእግዚአብሔር ታምኖ እነደኖረ ሁሉ በአስከፊውም ክፉ ወቅት የእግዚአብሔርን ታማኝነት እያሰበ በልበ ሙሉነት በእምነት ይቆማል ( ቁጥ 12 እና 13 ፤ ሌዋ 26 ፡ 40-45 ) ፡፡

እኛም ብንሆን ፡- በዚህ ምድር ባለን የህይወት ዘመናችን ሙሉ ለሙሉ ራሳችንን እግዚአብሔርን ከማያምኑ እና ከማያከብሩ ሰዎች ነጥለን ማኖር አንችልም ፡፡ የኛ የህይወት ውሳኔ እና ምልልስ ሌሎችን የሌሎችም የሕይወት ውሳኔ እና ምልልስ እኛን ተጽእኖ ውስጥ ያስገባናል ፡፡ ስለሆነም በማይገባን የተለያዩ መከራዎች ስናልፍ በፈጠረን እና በሚያኖረን አምላክ ታምነን በልበ ሙሉነት ልንቆም ይገባል፡፡ አሜን ፡፡

ተጨማሪ ምንባቦች

መዝ 27

ምሳ 3፡25-26

ኤፌ 3፡11-12

1ጴጥ 4 ፡17 -18

---------------- // ----------------

22/09/2022

ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።
1 ጢሞቴዎስ 4:16

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00