St. Paul Institute for Reproductive Health and Rights
21/11/2025
World Vasectomy Day Ethiopia 2025
ዛሬ የዓለም ቫሴክቶሚ ቀን ነው: : ቫሴክቶሚ ማለት የወንድ ዘር ማሰትላለፊያ ቱቦ በመቋጠር የሚሰራ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው።
ቫሴክቶሚ ለወንዶች አስተማማኝ፣ ከ99% በላይ ውጤታማ እና ቋሚ የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ነው እንዲሁም ወንዶች በስነተዋልዶ ጤና ላይ እና በቤተሰብ እቅድ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል::
ይህ ደሞ ጤናማ እና የተሻለ የታቀደ ቤተሰብ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ የስነ ትዋልዶ ጤና እንዲኖር አስተዋጾ አለው። ቫሴክቶሚ በተመላላሽ ክፍል የሚሰራ ፕሮሲጀር/ህክምና ሲሆን የጎንዮሽ ጉዳት የማስከተል እድሉ አነስተኛ ነው። ማገገሚያ ጊዜውም አጭር ነው። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም በአሁን ጊዜ በተለያዩ ዝቅተኛ እና መካከለኛ አገሮች እንዲሁም በአገራችን ኢትዮጲያ አገልግሎቱን ተጠቃሚ ማህበረሰብ ውስን ነው። የዓለም የቫሴክቶሚ ቀን በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ዘንድሮ በአርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። የበዓሉ አዘጋጀች ሴንት ፓል ኢንስቲትዩት ፎር ሪፕሮዳክቲቭ ሄልዝ ኤንድ ራይትስ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣ ማሪ ስቶፕስ ኢትዮጵያ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነበር የተዘጋጀው። የዚህ አመት መሪ ቃል "Mens Act of love towards their Partner" ሲሆን በቤተሰብ እቅድ ውስጥ የጋራ ሃላፊነት አስፈላጊነት እና በሥነ ተዋልዶ ጤና ውስጥ የወንዶች ተሳትፎ አስፈላጊነት ያጎላል።
ቫሴክቶሚ ወደፊት ልጅ መውለድ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ ለሆኑ ወንዶች ወይም ጥንዶች ተስማሚ የእርግዝና መከላከያ አማራጭ ነው።
ቫሴክቶሚ ሐኪምን ካማከሩ በኋላ በማንኛውም ሰዓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊሰራ የሚችል ህክምና/ፕሮሲጀር ነው።
ቫሴክቶሚን(vasectomy) ተመራጭ የሚያደርገው ምንድን ነው?ቫሴክቶሚ ወደፊት ልጅ መውለድ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ ለሆኑ ወንዶች ወይም ጥንዶች አስተማማኝ እና ውጤታማ የእርግዝና መከላከያ አማራጭ ነው።• ቫሴክቶሚ እርግዝናን በመከላከል ረገድ ወደ 100% የሚጠጋ ውጤታማ ነው።•ቫሴክቶሚ በተመላላሽ ክፍል የሚሰራ ፕሮሲጀር/ህክምና ሲሆን የጎንዮሽ ጉዳት የማስከተል እድሉ አነስተኛ ነው።•ቫሴክቶሚ ወንዶች በስነተዋልዶ ጤና እና በቤተሰብ እቅድ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል አማራጭ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |