DeritaTech Solution

DeritaTech Solution

Share

28/05/2026

Facebook , Instagram እና WhatsApp premium subscription !

ሜታ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከእስካሁኑ በማስታወቂያ ላይ ብቻ የተመሰረተው የገቢ ምንጭ ወጣ በማለት Facebook Plus ፣ Instagram Plus እና WhatsApp Plus የተሰኙ ና የሚከፈልባቸው ነገር ግን ተጨማሪ ፊቸሮች ያላቸውን Subscription tiers ይፋ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ለንግድ ተቋማት፣ ለይዘት ፈጣሪዎች እና ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ምርት ተጠቃሚዎች የሚሆኑ ተጨማሪ የክፍያ ዕቅዶችንም እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። ይህንን ተከትሎም የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ የ3% ጭማሪ አሳይቷል።

Facebook እና Instagram Plus ላይ ከተካተቱት አዳዲስ ፊቸሮች መካከል የተጠቃሚዎች Story ምን ያህል ግዜ በማን በተደጋጋሚ እንደታየ ማወቅ ማስቻል ፣ ያልተገደበ የስቶሪ ተመልካች ዝርዝር መፍጠር መቻል ፣ Story ከ24 ሰዓት በላይ እንዲቆይ ማድረግ ና ሌሎችም በርካታ ፊቸሮች አሏቸው።

WhatsApp Plus ላይ ካሉት አዳዲስ ፊቸሮች መካከል custom ringtones, additional pinned chats, list customization ና premium stickers ይገኙበታል።

የፌስቡክ ፕላስ ና ኢንስታግራም ፕላስ ተጠቃሚዎች በወር 3.99 ዶላር የሚከፍሉ ሲሆን የWhatsApp ተጠቃሚዎች ደግሞ የፕላስን ፊቸር ለማግኘት 2.99 ዶላር በወር ይጠበቅባቸዋል።

ሜታ ሁሉንም አዳዲስ የsubscription plans ሜታ ዋን (Meta One) በሚል በአዲስ ብራንድ ስር ለማጠቃለል ማቀዱም ታውቋል።

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa