yoseph_getamesay

yoseph_getamesay

Share

22/09/2023

Zetseat Yoseph. 5Months .girma_official

08/09/2022

!


ዮሴፍ ጌታመሳይ እባላለሁ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብ ታጥቤያለሁ! በመታደስ ድኛለሁ! #በክርስቶስ በመሆን #አዲስ #ፍጥረት ሆኛለሁ! ፀድቄአለው ፣ተቀድሻለው ፣ፍፁም ሆኛለው።

ሰማያዊውን ሀገሬን እየናፈቅኩ በዚህ በእንግድነት ምድር ስኖር የዳንኩበትን #የክርስቶስን ፍቅር ለሰዎች ሁሉ በመመስከር ሁሉም መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስለ ወንጌል በወንጌል እገድላለሁ!

በወንጌል ያገኘሁትን አርነት ለሁሉም እንዲደርስ አጋራለሁ፤ የኃጢአትን ይቅርታ ያገኘው #በክርስቶስ ፍፁም የተደረኩ ውድ ልጁ ነኝ!

ለየትኛውም እንቆቅልሽ እና ችግር ፍቺ እና መፍትሔ #ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ! ከኢየሱስ ውጭ የማወራለት ርዕስ የሌለኝ፥ ሰዎችን ሁሉ ስለ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብየ የምለምን የክርስቶስ እንደራሴ ነኝ!

#በክርስቶስ ነኝና መቼም ቢሆን ከሰው ሃሳብ፣ በሰው ሃሳብ ለሰው ሃሳብ አልቆምም! ሁልጊዜም #በክርስቶስ ሆኜ ከእግዚአብሔር ሃሳብ፣ በእግዚአብሔር ሃሳብ ለእግዚአብሔር ሃሳብ እቆማለሁ! ፍቅርን ለዓለም የምሰጥ እንጂ ጥላቻን ከዓለም የምቀበል አይደለሁም! ያለኝ ወንጌል የፍቅር ነው! ወንጌል ለዓለም ሁሉ ነው!

***
ቻሌንጁን በመቀላቀል እና ሌሎችን በመጋበዝ ዘላለማዊ ርዕሳችን የሆነውን #ኢየሱስን እናውራ! #በክርስቶስ ያለንን ማንነት እንናገር!!

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Kazanches
Addis Ababa
11223