YeneTech.com

YeneTech.com

Share

Photos from YeneTech.com's post 18/03/2025

°ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ዋለ፡፡

ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 9/2017 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችን ያሳተፈበት ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚገኙ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያ መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዓለም አቀፍ 114ኛ በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል'' በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ስኬታማ ወጣት ሴቶች ተሞክሮአቸውን ያካፈሉበት መርሀ ግብር ተከናውኗል፡፡

በዝግጅቱም የከተማችን ከፍተኛ ሴት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ጨምሮ 2000 በላይ ሴቶች የተገኙበት በተለያዩ ኪነጥበብ ክንዋኔዎች ተዘጋጅቶ ታላላቅ እንግዶች በተገኙበት የተሳተፉበት የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

ዘንድሮ በዓሉ በሀገራችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶ ተሳትፎ ይረጋገጣል " በዓለም ዓቀፍ ደረጃ For All Women And Girls Rights: Equality Empowerment!" በሚል መሪ ሀሳብ ሲከበር በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማናቸዉንም ብሎም ሴቶችን ማብቃት ከመቸዉም በላይ ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባዉ አጀንዳ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨመረሻም በዘርፍ ያሉ የክፍለ ከተማ ሰዎች በሴቶች ላይ አተኩሮ የተከረው አከባበር በነበራቸው ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡ በልዩነት ደግሞ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰርፍኬት ተረክበዋል፡፡

Photos from YeneTech.com's post 18/12/2024

የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ታቦተ ህግ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል!!

ላለፉት ሁለት አመታትና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ጊዜያት እድሳት ሲደረግለት የቆየው የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እድሳት ወደ መገባደዱ መድረሱን ዛሬ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም. በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።

የካቴድራል የዕድሳት እና የጥገና ስራ ከተጀመረ 773 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በየጊዜው በገጠመው የሲሚንቶ ችግር እና ሌሎችም ሁነቶች ምክንያት ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱን ተጠቁሟል።

የህንጻውን ግንባታ ለሚያከናውነው ኮንትራክተር እስካሁን ድረስ ከ124 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ እንደተከፈለው የተነገረ ሲሆን ቀሪ ክፍያ እንደሚቀረው ነው የተገለጸው።

ታቦተ ህጉ በተባለው ቀን ወደ መንበሩ ለማስገባት ለኮንትራክተሩ የሚከፈለው ከ47ሚሊዮን ብር በላይ ህዝበ ክርስቲያኑ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ተደርጓል።

የቤተክርስቲያን ህንጻው ግንባታ ሂደት 95 በመቶ ደርሷል።

የቤተክርስቲያኑ እድሳት ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ አገልግሎቱ ባሻገር ትልቅ ሃገራዊ አበርክቶ ያለውን ካቴድራሉን እና ቅርጻቅርጾቹን ኪነ ጥበባዊና ቅርሳዊ ይዞታቸውን በጠበቀ መልኩ መታደሱንም ተነግሯል።

የአጼ ኃይለ ስላሴን የንግስና በዓለ ሲመት ያስተናገደው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የመሪዎች፣ የጀግኖች አርበኞች እና የታዋቂ ሰዎች ዘላቂ የማረፊያ ስፍራ ነው፡፡ በብዙዎች ይጎበኛልም፡፡

የካቴድራሉ ግንባታ በ1922 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን በፋሽስት ጣሊያን ወረራና በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ በ1936 ዓ.ም. መጠናቀቁን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

08/09/2024

የድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ሙዚቃ ጳጉሜ አምስት (62) አመት ይደፍናል፡፡
(ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)

ተወዳጁ ሙዚቀኛ እና የስፖርት ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ከበርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎች ውስጥ የኔ ሐሳብ የተሰኘ ሙዚቃ (62) አመቱን ጳጉሜ 5/2016 አመት ምህረት ይደፍናል፡፡

ዘመን ተሻጋሪ የሆነው በዚህ ልክ በትዝታ ማዕበል እያተከዘ በብዞዎች ልብ ውስጥ የተቀመጠ "የኔ ሐሳብ" ሙዚቃ የተለያዩ ወጣት እና አንጋፋ ሙዚቀኞች ይንን ሙዚቃ በራሳቸው ቀለም አቀንቅነዋል::

ከነዛም ውስጥ ሙገስ መብራቱ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ ሚካኤል ለማ ደምሰው እና ሌሎችም ጎሮሮአቸውን ለመፈተን በዚህ ሙዚቃ እራሳቸውን ይለኩ ነበር፡፡

የዚህ ሙዚቃ የግጥም ደራሲ ጌታቸው ደባልቄ የዜማ ደራሲ ካሳ ወልዴ አቀናባሪው መርሲ ናልባልዲያን፡፡

ሙዚቀኛ ጋሽ ግርማ ነጋሽ ለዚህ ሙዚቃ ሲናገር "የኔ ሀሳብ ሁሌ እንዳማረባት እኔንም እየጦረች እዚህ አድርሳኛለች'' ብለዋል፡፡

የሙዚቃ ቪድዮ የተሰራበት አጋጣሚ ሲያወጉ "አምሳለ ገነት ይመር የምትባል የወጋየሁ ንጋቱ ባለቤት እሷ ሸምገል እያልን ስንሄድ ፈራች እና አንድ ነገር ተቀርፆ እንዲቀመጥ ሀሳብ ታቀርባለች እኔ ደሞ ይንን ሞያ ሸሽቼ ማለት ቤተሰብ ስላስቸገረኝ… እኔ ራድዮ ጣብያ ነበር ምሰራው በምስራበት በወቅት መጥታ የሬድዮ ጣብያ አለቃዬን አስፈቅዳ ይዛኝ ሄደች ነገሩ እንግዲህ አፍ እያነቃነቁ የሚዘፍኑት "ማይም " አይደል ሚባለው እንደሱ ልንሰራ ነው የሄድነው፡፡ ግን አንድ ያላሟላችሁ ነገር ነበር …እሱ የምንቀዳበት ቴፑ ባትሪ መኖር ነበረበት ግን ባትሪ የለውም😂 ባትሪ ሲኖር ያው ለመስራት ያመች ነበር፡፡

የምንሰራበት ቦታ ስንደርስ ሲታይ ባትሪ የለውም ስለዚህ አማራጭ ያደረግነው እዛው ቢሮ ሬድዮ ጣብያ አካባቢ መስራት ነው አሁን የምታዩት ቪድዮ በዚህ መልክ ተሰርቷል "ብለዋል፡፡

ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ የኔ ሀሳብ ሙዚቃ ተሰርቶ አልቆ ከሌሎች የሙዚቃ ሰዎች ጋር ሙዚቃው ተወዳድሮ " ሶስት መቶ ብር" እንዳሸነፉ እና ለራሳቸው "አምሳ ብር" ወስደው ቀሪውን ሙዚቃውን ለሰርሩት እንደሰጡ ጨምረው እንደገለፁ ይጠቁማሉ፡፡

የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት እጅጉኑ ያከብሮታል ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ፡፡

25/08/2024

በርካታ ፊልሞች ላይ የምናውቀው ተዋናይ ጌታቸው (ባቡጂ) ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

ለቤተሠቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa