Amaizing GRACE
15/11/2025
✔️የመቅደሱ መድረክ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን
የሚሰበክበት መደረክ ነው። #የአዳራሽ #መድረኮቻችንስ?
✔️በቤታቸውም ቢሆን የሚሰበከው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
#በእኛ #ቤትስ?
✔️በመቅደሱና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰበከው
ከስንት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ዕለት ዕለት ነው።
#እኛስ?
✔️ዕለት ዕለት መተው የሚያቅታቸው ነገር ቢኖር ስለ ኢየሱስ
መስበክና ማስተማር ነበር። #እኛስ?
✔️ሐዋርያቱን እንደዚህ ያደረጋቸው ምንድን ነው ብየ ሳስብና ስጠይቅ ወደ ልቤ የመጣው ምላሽ ምዕራ 2 ላይ የወረደባቸው መንፈስ እና ምዕራፍ 4 ላይ በድጋሚ ደግሞ የተሞሉት የመንፈስቅዱስ ሙላት ነው የሚል ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እኔና እናንተም በመንፈስቅዱስ ሃይል መሞላት ይሁንልን።
✔️በዚህ መጨረሻ ዘመን በቀረልን ጥቂት ዘመን ስለ ሌላ ነገር መስበክ፣ ማስተማር፣ መዘመር እና መወያየት ትተን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንስበክ፣ እናስተምር፣ እንዘምር ደግሞም እንወያይ።
👉ምን ትላላችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ? ጥቅሱ አይጠርማችሁም?
17/10/2025
👉በቅድሚያ ከታች የተቀመጡትን ሁለቱን ፎቶዎች ለተወሰኑ ሰከንዶች ሁለቱንም ለየብቻ ተመልከት።
👉ከተመለከትክ ሦሰት ጥያቄዎችን ልጠይቅህ መልሱን በራስህ አእምሮ ያዝ።
ጥያቄ 1፦
ይበልጥ የሳበህ የትኛው ፎቶ ነው?
ጥያቄ 2፦
የመጀመሪያውን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ ያረፈው ከልጅቷ ፎቶ ላይ ወይስ ከጀርባ ካለው ተፈጥሮ ላይ ወይስ ከሁለታቸው ላይ?
ጥያቄ 3፦
ሁለተኛውን የልጅቷን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ የት ላይ ወደቀ?
👉ምናልባት ትክክል ከሆንኩ የመለስካቸውን በአእምሮህ ውስጥ ያሉትን መልሶች ልንገርህ። የመረጥከውና ይበልጥ የሳበህ ፎቶ ሁለተኛው የልጅቷ ፎቶ ነው።
👉የመጀመሪያውን ፎቶ ስታይ ትኩረትህ ከአንዳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ከሁለቱም ላይ አርፏል። ይህ ማለት ከልጅቷ መልክና ከልጅቷ ጀርባ ካለው ተፈጥሮ (እጽዋት) ላይ አተኩረሃል ማለት ነው።
👉ሁለተኛውን ፎቶ ስታይ ደግሞ ትርጉም የሚሰጥ ሌላ ነገር ስለሌለ ትኩረትህ የልጅቷ መልክ ላይ ብቻ ሆኗል።
ትክክል ነኝ አይደል? Thank you
ዋናው መልዕክት፦
ሁለቱም የልጅቷ ፎቶዎች ናቸው። ነገር ግን ሁለተኛው በ Editing ተሰራና ከጀርባ ያለው ተፈጥሮ Blurred እንዲሆን (እንዲደበዝዝ) ተደረገ። Blurred መሆን ማለት ከልጅቷ ጀርባ የሆነ ነገር አለ ግን ምን እንደሆነ እንዳይታወቅ ተደረገ ማለት ነው።
በ Editting ይህ የተደረገበት ሁለት አላማዎች አሉ፦
✔️የመጀመሪያው አላማ፦ የልጅቷ ውብ መልክ ብቻ ጎልቶ እንዲታይ ስለተፈለገ ነው።
✔️ሁለተኛው አላማ፦ ደግሞ ሰዎች አንድም ሳያስቀሩ ሙሉ ትኩረታቸውን በልጅቷ መልክ (ውበት) ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ስለተፈለገ ነው። 100% ልጅቷ ላይ እንዲያተኩሩ ተፈልጓል።
👉ልክ እንደዚሁ የክርስቶስ አገልጋዮች Blurred (መደብዘዝ) አለባቸው። አላማውም፦ በእነርሱ ላይ ያለው የክርስቶስ መልክና ውበት ብቻውን ጎልቶ እንዲወጣና እንዲሁም ሰዎች ሁሉ እነርሱ በሚሰብኩትና በሚያገለግሉት ክርስቶስ ላይ ብቻ ትኩረታቸውን እንዲጥሉ ለማድረግ ነው። እውነተኛ የክርስቶስ አገልጋይ እርሱ ደብዝዞ ክርስቶስን ብቻ የሚያሳይ እንጅ ከክርስቶስ ጋር እኩል (ሃምሳ ሃምሳ) ደምቄ ልታይ የሚል አይደለም። የማገለግላቸው ሰዎች ትኩረታቸውን በክርስቶስ ላይ ብቻ ሳይሆን በእኔም ላይ ማድረግ አለባቸው የሚል አይደለም። እሱም ይታይ እኔም ልታይ የሚል አይደለም።
👉ተፈጥሮው እኛን አገልጋዮችን ቢወክል የልጅቷ መልክ ደግሞ ክርስቶስን ቢወክል ዋና መልዕክቱ እኛ እንደተፈጥሮው እንደብዝዝና ክርስቶስ እንደ ልጅቷ ጎልቶ ይታይ የሚል ነው። ሲቀጥልም እኛ እንደተፈጥሮው እንደብዝዝና የሰዎች ትኩረት እንደ ልጅቷ በክርስቶስ ላይ ብቻ ይሁን የሚል ነው።
👉በአጭር ቃል በእኛ ላይ ያለ አስደናቂ መልክ (ክርስቶስ) ስላሉ ለሰዎች ሁሉ እሱን አጉልተን ለማሳየት Blured እንሁን። እዩት እዩት እንጅ እዩኝ እዩኝ አንበል። እወቁት እወቁት እንጅ እወቁኝ እወቁኝ አንበል።
👉በ1ኛ ጢሞ 3:16 ላይ እግዚአብሔርን የመምሰል ታላቅ ሚስጥር ማለት በአጭሩ በስጋ የተገለጠውን፣ በመንፈስ የጸደቀውን፣ ለመላዕክት የታየውን፣ በአህዛብ የተሰበከውን፣ በአለም የታመነውንና በክብር ያረገውን ክርስቶስን መምሰል ማለት ነው። የክርስቶስ መልክ በእኛ ሙሉ በሙሉ ሲታይ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ወደ መምሰል መጣን ማለት ነው። ይህ እግዚአብሔርን የመምሰል ሚስጥር ደግሞ ዕለት ዕለት የምንለማመደው እንደሆነ ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞ 4:7-8 ላይ ጢሞቲዎስን "እግዚአብሔርን ለመምሰል ራስህን አስለምድ" ከሚለው ተነስተን መረዳት እንችላን። ለአሁኑና ለሚመጣው አለምም ተስፋ ያለውና ለነገር ሁሉ የሚጠቅም እንሆነ ቀጥሎም ይናገራል።
ማጠቀለያ፦ Blurred (እንደብዝዝ) እንሁን እና ክርስቶስ ብቻ በእኛ ላይ ይታይ። የሰዎች ትኩረት ሁሉም በእርሱ ላይ ብቻ ይሁን። አሜንንን
Andu in Christ
16/07/2025
👉የተከፈለልህን አሜን ብለህ በእምነት ተቀብለህ ከማረፍ እና የከፈለልህን አካል ከማመስገን ይልቅ የማትችለውን በራስህ ጥረት ለመክፈል መግደርደር፣ መሯሯጥ እና መድከም #ትዕቢተኝነትህን ያሳያል። እግዚአብሔር ደግሞ ትዕቢተኞችን ይቃወማል። ስለዚህ በራስህ ለመጽደቅ ያለህን ከንቱ ጥረት ተወውና የእግዚአብሔር ነጻ የፍቅር ስጦታ በእምነት አሜን ብለህ ተቀበል።
👉የዘላለም ሞት ሊከፍልህ ቀን እየጠበቀ ያለው የሃጢአት ዕዳህ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሙሉ በሙሉ ከፍሎታል። አሜን ብለህ ከልብህ #በእምነት #ብቻ ስተቀበል የተከፈልህ በአንተ ላይ በፀጋ ይቆጠርልሃል።
👉እኔ የተከፈለልኝን አሜን ብየ በእምነት ተቀብየ በነጻነት፣ በሰላም፣ በእረፍት እና በጸጋ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር ከጀመርኩ 16 አመታት አልፈዋል። ክብር ሁሉ ሃጢአትን ማስወገድ የሚችለውን ብቃት ያለውን የመስዋዕቱን በግ (ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን) ለሰጠን ለእግዚአብሔር አብ፣ በራሱ ፈቃድ ራሱን በፍቅር ለአባቱ አስገዝቶ ወደ ምድር በስጋ በመምጣት በመስቀል ላይ ለታረደልን ለእግዚአብሔር ወልድና ክርስቶስ በደሙ በዋጃት በክርስቶስ አካል ውስጥ ላለው የርስታችን መያዣ ለሆነው ለእግዚአብሔር መንፈስ (ለመንፈስቅዱስ) ራሱን በሶስት አካላት ለገለጠው ለአንዱ አምላክ ይሁን። አሜንንን
Click here to claim your Sponsored Listing.