HUDA

HUDA

Share

01/03/2025

±ምሥጢረ ዓድዋ + ያነበበ ሸር

በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

~ቤት ያለ መሰረት አይሰራም
ዓድዋ ቤት ናት
መሰረቷ ግን አጼ ሚኒሊክ ናቸው
መሰረቱን የጣለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

~ቤት ያለ ምሰሶ አይቆምም
ዓድዋ ቤት ናት
ምሰሶዋ ግን አጼ ሚኒሊክ ናቸው
ምሰሶውን የተከለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

~ሥጋ ያለ ነፍስ አትቆምም
ዓድዋ ሥጋ ናት
ነፍሷ ግን ሚኒሊክ ናቸው
ነፍስና ሥጋን ያስማማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው
አጥንቷ ነጻነት ነው
ደሟ የሀገር ፍቅር

~መዓር ያለ ንብ አይገኝም
ዓድዋ መዓር ናት
ንብ ግን አጼ ሚኒሊክ ናቸው
መዓር ቆራጬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው
ቀፎው ጣሊያን ነው
መዓሩ የተቆረጠበት ጭሱ የካሀናት ጸሎት ነው

~ኳስ ጨዋታ ያለ ጎል ውጤት የለውም
ዓድዋ ኮስ ጨዋታ ናት
ጎሉ ግን አጼ ሚኒሊክ ናቸው
ዳኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው
ደጋፊዎች አሉላ እና ጣይቱ ናቸው
ጨዋተው ጦርነት ነው
ሜዳው ነጻነት ነው

~ዓይን ያለ ብሌን አታይም
ዓድዋ ዓይን ናት
ብሌኗ ግን እቴየ ጣይቱ ናቸው
ማየት የማይችለው ነጩ ጣሊያን ነው

~ዓድዋ ፀሐይ ናት
ብርሃኗ እቴዬ ጣይቱ ናቸው
ፀሐይ የወጣችበት ሰማይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

~ዓሳ ያለ ውሃ አይኖርም
ዓድዋም ያለ እቴዬ ጣይቱ የለችም
የውሀው ባህር ነጻነት የሀገር ፍቅር ነው

~ደም ያለ ልብ አይኖርም
ዓድዋ ደም ናት
ልብ ግን እቴዬ ጣይቱ ናቸው
የደም ስሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

~አካል ያለ ራስ አይኖርም
ዓድዋ አካል ናት
ራስ ግን እቴዬ ጣይቱ ናቸው
አንገት ነጻነት ነው

~ዓድዋ ልጂ ናት
አባቷ ሚኒሊክ ናቸው
እናቷ ግን እቴየ ጣይቱ ናቸው
ሞግዚቷ ቅዱስ ጊዮርጊስ ናቸው

~ዓድዋ ዛፍ ናት
ግንዷ አጼ ሚኒሊክ ናቸው
ስሯ እቴዩ ጣይቱ ናቸው
ቅርጫፏ ሰራዊተ ሚኒሊክ ናቸው
ለምለሙ ቅጠሏ ነጻነት
ጥላዋ የሀገር ፍቅር
ፍሬዋ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅርፍቱ ጣሊያን

መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Adis Abebea
Addis Ababa
1974