Fikiru Kumera
21/03/2024
"ብልፅግና ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል በመጠበቅ ለሁሉም የምትመች ሀገር እየገነባ ነው"
አቶ ብርሀኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
መጋቢት 12/2016 ዓ.ም የካ ወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን
የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ከክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር ሲያካሂድ የቆየውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መርሀ ግብር በማካሄድ ላይ ነው።
19/03/2024
18/03/2024
ፓርቲያችን ብልጽግና መሰረቱ ሰው በመሆኑም ለህዝብ የገባውን ቃል የሚያከብር የሚፈጽምም ነው። በዚህም በርካታ ሰውተኮር ተግባራትን በስኬት በመፈጸም የማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል። ፓርቲያችን እያስመዘገባቸው የሚገኙትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድሎች አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ የምርጫ ጊዜ ለህዝብ የገባቸውን ተግባራት በቁርጠኝነት ለመተግበር ከመላው አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በየካ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ወረዳዎች በሁሉም መሰረታዊ ፓርቲ አመራሮች ሲካሄድ የነበረው የመሰረታዊ ፓርቲ ኮንፈረንስ ሂደት ከወረዳ አስተባባሪዎች ጋር ተገምግሟል።
በግምገማ መድረኩም የክ/ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መገርሳ ገላና እንደገለፁትበፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ላይ በተቀመጠው መሰረት የተካሄደው የአባላት ኮንፈረንስ በመሰረታዊ ድርጅት በድምቀት እንደተካሄደ ገልፀው በቀጣይ በወረዳ ደረጃ ለሚካሄደው መድረክ ቅድመ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
እየተደረገ ባለው የመላው አባላችን ኮንፈረንስ ላይ የተጀመሩ የልማት ኢንሸቲቮችን በማጠናከር በተለይም በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ ስንዴና እንሰሳት እርባታ ስራዎችን እናስቀጥላለን። የፓርቲያችንን ህዝባዊ ቅቡልነት በማጽናት ጉድለቶችን እያረምን ቀሪ ተግባራት በትኩረት በመፈጸም የስራ ዕድልና የልማት ስራዎችን በማስቀጠል በብሔራዊ ገዥ ትርክት አንድነታችንን እያፀናን ህብረብሔራዊ የመደመር ጉዟችን እንደሚቀጥል ማረጋገጥ ተችሏል።
በአጠቃላይ በከተማችን ብሎም በየካ ክ/ከተማ ሁሉም ወረዳዎች እየተካሄደ በሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረስ ፓርቲያችን የጀመረው የሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ በማስቀጠል ህዝብ የሰጠውን አደራ በብቃት ለመፈጸም ቃልን ማደስ የተቻለበት አውድ ተፈጥሯል። የህዝብን ድምጽ በማክበር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍተታና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የጽንፈኝነት አስተሳሰብን በመታገል የሰላም ዕሴቶቻችንን ጠብቀን ከነጠላ ዕውነት ወደወል ዕውነት በመሻገር ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በመትከል ሀብቶቻችንን በአግባቡ በመጠቀምና በማስተዳደር ከዕዳ ወደምንዳ የሚደረገውን ብልጽግናዊ ጉዞ ለመፈጸም ቃልን ያደሰበት ሆኗል።
14/03/2024
ለከተማችን ትልቅ የምስራች እነሆ!
በ100 ሺሕ ካሬ ሜትር ስፍራ ላይ ያረፈው የሴቶች የተሀድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል።
ማዕከሉ በዋነኛነት በሴተኛ-አዳሪነት ላይ የተሰማሩ ሴቶችን በመቀበል ሙያዊ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ፣ ክትትልና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ስራ እንዲሰማሩ የሚያደርግ ሲሆን፣ በአንድ ዙር ብቻ 10,000 ሴቶችን ተቀብሎ የማሰልጠን አቅም አለው።
ወጣት ሴቶቹ በማዕከሉ ቆይታቸው ከሚያገኙት የስነ ልቦና ድጋፍ በተጨማሪ በስነ-ውበት፣ በከተማ ግብርና ፣ በምግብ ዝግጅት፣ በከተማ ውበት አጠባበቅ፣ በኮምፒዩተር ሙያ፣ በሞግዚትነት፣ በመስተንግዶ፣ በፀጉር ስራ፣ በኤሌክትሪክና ሸክላ ስራ፣ በእንጨት ስራዎች፣ በልብስ ስፌት እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች በቂ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የምናደርግ ይሆናል።
ከዚህም በተጨማሪ ማዕከሉ ምቹ የመኝታ ክፍሎች፣ ቤተ-መጻህፍት፣ የቤት ውስጥ ስፖርት ማዘውተሪያ ጂምናዚየም፣ ምቹ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቅም የተደራጀ ዘመናዊ የህክምና ማዕከል፣ የተግባራዊ ልምምድና የሰርቶ ማሳያ ማዕከላት፣ የልብስ ንጽህና መጠበቂያ ላውንደሪዎች፣ የህጻናት ማቆያና እንክብካቤ ማዕከላት፣ የህጻናት ስነ-አዕምሮአዊ እድገት ክትትልና ልህቀት ክፍል እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች የተካተቱበት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ከተማን ለመገንባት ለህዝባችን የገባነውን ቃል እየፈጸምን አሁንም የመረጠንን ህዝብ በታማኝነትና በትጋት ማገልገላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
Magaalaa keenyaaf misiraachoo guddaan kunoo!
Giddugalli haaromsaa fi dandeettii dagaagsuu dubartootaa lafa kaaree meetira kuma 100 qabate tajaajilaaf banaa ni taasifama.
Giddugalichi irra caalaa dubartoota daldaala saal-qunnamtii irratti bobba'an simachuun hordoffii fi leenjii deeggarsa ogummaa fi qor-qalbii akka argatan taasisuun gara hojiitti akka bobba'an kan taasisu yoo ta'u, marsaa tokko qofaatti dubartoota 10,000 simachuun dandeettii leenjisuu qaba.
Dubartoonni dargaggoonni turtii isaaniitiin deeggarsa qor-qalbii argatan cinaatti miidhaginaan, qonna magaalaan, qophii nyaataan, eegumsa miidhagina magaalaan, ogummaa kompiitaraan, kununsa daa’immanii, keessummeessuun, hojii mana rifeensaan, hojii elektirikaa fi supheen, hojii mukaan, hodhaa huccuu akkasumas dameewwan hojii biroon leenjii gahaa kennuun gara hojiitti akka bobba’an kan taasisu ta'a.
Kanatti dabalees giddugalichi kutaa ciisichaa mijataa, mana kitaabaa, jiiminaaziyeemii hojii ispoortii mana keessaa, galma soorataa mijataa, bilcheessa nyaataa ammayyaa, giddugala yaalaa ammayyaa dand
05/03/2024
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል። ግምገማው አራቱን የአስተዳደርና ፍትህ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በተመለከተ በቀረቡ አፈፃፀሞች ላይ በማተኮር ተጀመሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሰል የግምገማ መድረኮች በመንግሥት ተቋማት የመፈፀም ባህልን ለማዳበር የጀመሯቸው መሆናቸው ይታወሳል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Ababa