Abrehot Library
29/05/2026
በአብረሆት ቤተ መጻሕፍት ለሠራተኞች የተሰጠ የካይዘን (Kaizen) ሥልጠና በምስልና ገለፃ 🚀
ካይዘን (ዘላቂነት ያለው መሻሻል) ከጃፓን የመነጨ ጠንካራ የሥራ እና የሕይወት ፍልስፍና ሲሆን፣ በአብረሆት ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ይህንኑ መልካም ተጽዕኖ ለማምጣት ስልጠናው በተለያየ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች በመሰጠት ላይ ይገኛል። ስልጠናው በካይዘን ፍልስፍና ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሀሳቦች ይዳስሳል ከነሱም :-
🧩 አራቱ የለውጥ ምሰሶዎች
የሁልቀን (Every Day)፦ ማሻሻል የዕለት ተዕለት ተግባር ነው።
የሁሉም ሰው (Everyone)፦ እያንዳንዱ ሠራተኛ ይሳተፋል።
የሁሉም ቦታ (Everywhere)፦ በሁሉም የቤተ መጻሕፍቱ ክፍሎች ይተገበራል።
የሁሉም ነገር (Everything)፦ እያንዳንዱ የሥራ ሂደት እና አገልግሎት ይሻሻላል።
⚙️ 5ቱ መሠረታዊ ባህሪያት
ተሳትፎአዊ፦ ሁሉንም ሠራተኛ ያሳትፋል።
ዘላቂነት ያለው፦ የማይቋረጥ አዎንታዊ ለውጥ ነው።
የጥቂት በጥቂት ድምር፦ በጥቃቅን እርምጃዎች ትልቅ ስኬት ያመጣል።
ያለ ከፍተኛ ወጪ፦ ከፍተኛ የገንዘብ ኢንቨስትመንት አይጠይቅም።
ተለዋዋጭ፦ በማንኛውም የሥራ ሁኔታ ውስጥ የሚተገበር ነው።
በአጠቃላይ የአመራር እና የሠራተኛ ትኩረት ምን መሆን እንዳለበት ማለትም ነባራዊ ሁኔታን መረዳት ፣ የሥራ አካባቢን ማሻሻል(ምቹ እና ቀልጣፋ የሥራ ቦታ መፍጠር) ፣ የሰውን ኃይል በአግባብ የሥራ ቦታ ማዋል ፣ ሠራተኛውን የለውጥ ዋና አንቀሳቃሽ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው ።
29/05/2026
ሳምንታዊ ጥያቄ
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍትን በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ይጠቀማሉ?🤔 መልሳችሁን በኮመንት ላይ አስቀምጡ 💫
1. በየቀኑ! 📖
2. በየሳምንቱ! 🎒
3. በየወሩ! 📚
26/05/2026
📚 የአብርሆት ቤተመጻሕፍት የመጻሕፍት ስጦታ ለዳሪያን ማህበረሰብ!
የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በቦታው ድረስ በመሄድ ለዳሪያን ማህበረሰብ ቤተመጻሕፍት (Community Library) 2,000 መጻሕፍትን አስረክቧል።
በእለቱም የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የቤተመጻሕፍት ኮሚቴ፣ የከተማው ከንቲባ እና የትምህርት ቢሮ አመራሮች በጋራ በመሆን ደማቅ የንባብ ቀን ፕሮግራም አክብረዋል። ማራኪ የሆኑ ግጥሞችና መነባንቦች ለታዳሚው ቀርበዋል። በ1ኛ እና 4ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የንባብ ውድድር ተካሂዶ፣ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የዳሪያን ማህበረሰብ በአጠቃላይ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ለትውልድ ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናቸውን በስጦታ አቅርበዋል።
📖 "ንባብ ለትውልድ ግንባታ!"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 00:00 |