Awusa.com
10/05/2026
"የሰላሙ ስምምነት የሁለቱም ወገኖች አስገዳጅ ምርጫ ነበር" - ዳንኤል ብርሀነ
ደብረጽዮን በፕሪቶሪያ የክህደት ድርጊት እንደተፈጸመ ሊያሳምነን ይፈልጋል። ጌታቸው በበኩሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የተፈረመው "ወሳኝ ሽንፈት" ሊያጋጥም ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት እንደነበር ሊያሳምነን ይጥራል።
እውነታው ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት የነበረውን እልቂት ያስቆመና ሁለቱም ወገኖች እንዲሁም አስታራቂዎቹ ቁርጠኛ ቢሆኑ ኖሮ ወደ ዘላቂ የሰላም መፍትሔ ሊያመራ የሚችል ዕድል የነበረው መሆኑ ነው።
ነገር ግን ማንኛውም የተኩስ አቁም ስምምነት በቸርነት የሚሰጥ ስጦታ አይደለም። ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን አጥብቀው የሚፈልጉበት አስገዳጅ ሁኔታ ላይ ነበሩ፤ ይህም ለማንኛውም የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያውና መሠረታዊው መመሪያ (ABC) ነው።
ስለዚህ ደብረጽዮን እና ጌታቸው ያለፈውን ታሪክ መከራከሪያ ማድረጋቸውን አቁመው መምራት ላይ ቢያተኩሩ ይሻላል—እርግጥ መምራት የሚችሉ ከሆነ።
Daniel Berhane-
09/05/2026
📍ህወሓት በአክሱም ሙስሊሞች ላይ በአዲስ መልክ አፈና ጀምሯል!
በትግራይ ክልል የእስልምና እምነት ተከታዮች ከህወሓት ቡድን ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸዋል፡፡ በክልሉ ሂጃብ መልበስ ፣ በጋራ መስገድ ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በተደጋጋሚ ጊዜ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አፈናዎችን ይፈፅማል፡፡ በተለይም የአክሱም ሙስሊሞች የመስገጃ ቦታ የላቸውም፣ ትምህርት ቤቶች ሂጃብ የጠመጠመችን ተማሪ ወደትምህርት ቤት አያስገቧትም፡፡
ይህ ሁኔታ ለረዥም ጊዜ በአክሱም ሰፍኖ የቆየ ሲሆን ሰሞኑን ቡድኑ በአዲስ መልክ በጀመረው አደገኛ እንቅስቃሴ በርካታ የእምነቱን ተከታዮች አፍኗል፡፡ በመንገድ ላይ በሚያገኛቸውን የእምነቱ ተከታዮች ላይ ዛቻ እያደረሰ ነው፡፡ አፈናው በትምህርት ቤቶች ላይም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ህወሓት በመላው የትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀው ጦርነት እንዳለ ሆኖ ሙስሊሞችን ለይቶ የማጥቃቱ ነገር በግልፅ ተጀምሯል፡፡
እንግዲህ በሙስሊም ጠላትነቱ አለቃው ኢሳያስ አፈወርቂም የሚታወቅ ሲሆን አሽከሩ ህወሓትም ይህኑን በመተግበር ክልሉ ለሙስሊሞች የስቃይ ምድር እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡
04/05/2026
🇪🇹👌
ጀግናው የኢፌድሪ አየር ሃይል የታጠቃቸው አዳዲስ በአምስተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ የዘመኑ፣ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ፣ ሁሉንም የአየር ሆኔታ የሚቋቋሙ፣ እንዲሁም ከአየር ወደ አየር የሚደረጉ የመከላከያ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚችሉት፣ ውጤት ቀያሪወቹ SU-35 Fighter Jet ተዋጊ ጀቶች በዛሬው እለት በአፋር ክልል የተሳካ የበርሃ አየር ሙከራ አድርገዋል።
ከ ሚግ 21 ውጭ ምንም የማያውቁ ቆሞ ቀሮች ያለ አቅማቸው ከኢትዮዽያ ጋር ትካሻ መለካካቱን ቢያቆሙ ይበጃቸዋል!!
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.